✞ በዓለ መስቀልን ምክንያት በማድረግ ከብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ✞ በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፥ አደረሰን! ለዛሬ ንዑድ ክቡር ከሚኾን ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ያደረግሁትን [ምናባዊ] ቃለ መጠይቅ እጋብዛችኋለሁ፤ መልካም ቆይታ! #ጥያቄ፡- አባታችን በመጀመሪያ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለልጆችህ ምዕዳን ለመስጠትና ለምንጠይቅህ አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ ትሰጠን ዘንድ ፈቃድህ ስለ ኾነ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፤ […]

Continue reading

መስከረም17፡ቀን (27 Sept 2018)

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።         *መስከረም17፡ቀን *እንኳን፡ለጌታችን፡ለአምላካችን፡ለ­መድኃኒታችን፡ለኢየሱስ፡ክርስቶስ፡­የመስቀል፡በዓል(የጻድቁ፡ንጉሥ፡የቆስጠንጢኖስ፡እናት፡ንግሥት፡ቅድስት፡ዕሌኒ፡ከተሠወረበት፡በደመራ፡ጢስ፡ቦታው፡ከተገለጠላት፡በኋላ፡ቁፍሮ፡ያስጀመረችበት፡ነው)በሰላም፡አደረሰን­።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡ከሚታሰቡ፡­የከበረች፡ሮማዊት፡ታኦግንስጣና፡ከ­ሊቀጳጳስ፡ከአባ፡ዲዮናስዮስ፡ከዕረፍታቸው፡በዓል፣ከሊቢባ፣ከኪርያኖስ፣ከዮስጢናና፡ከቴክሴልጥስ፡ከመታሰቢያቸው፡ረድ­ኤትና፡በረከትት፡ያሳትፈን። *”ሚመጠነ፡ሀብተ፡ጸጋ፡ተውህለ፡ለክብር፡ዕፀ፡መስቀል።መስቀልከ፡ንዋየ፡ሐቅል፡ለፀብእ፡ወሰይፈ፡መለኮት፡ዘሐራ፡ዚአከ።መስቀልከ፡ገፍታኤ፡ማዕከል፡እንተ፡ጽልእ፡ወነሳቴ፡ጥቅም፡ዘኃጣውእ።መስቀልከ፡አብ፡ለእጓለ፡ማውታ፡ወመኰንኖሙ፡ለዕቤራት።መስቀል፡መርስ፡ለእለ፡ይትመነደቡ፡በባሕር፤ወመርሶ፡ለእለ፡ይሳኵዩ፡ውስተ፡በደው።መስቀል፡መርሐ፡ዕውር፡ወምርጉዘ፡ሐንካሳን፡ወኃይሎሙ፡ለፅቡሳን።መስቀልከ፡ዕፅ፡ዘያልሕቅ፡ሕፃናተ፡መሃይማናን፡በአጥባተ፡ቅድስት፡ቤተ፡ክርስቲያን።መስቀልከ፡አክሊለ፡ነገሥታት።መስቀልከ፡ትምክህቶሙ፡ለመሲሐውያን።መስቀልከ፡ዘይሴርዎሙ፡ለመሠርያን፡ወይዘርዎሙ፡ለመሰግላን።መስቀልከ፡ሰያሚሆሙ፡ለካህናት፡ወአሳዬ፡ሩጸቶሙ፡ለዲያቆናት።መስቀልከ፡ዘያነሥኦሙ፡ለውዱቃን፤ወያረውጾሙ፡ከመ፡ኀየል፡ለፅውሳን።መስቀልከ፡ዘኮነ፡ሕፄሃ፡ለመርዓት፡ወሕዳጋቲሃ፡ለእንተ፡ደኃርካ፡በምኵራብ።መስቀልከ፡መሠረተ፡አሚን፡ወዓምደ፡ሃይማኖት፡ለእለ፡ይትዌከሉ፡ቦቱ።መስቀልከ፡መብጠሌ፡ኵሉ፡ስራይ፡ወመፅርዔ፡ኵሉ፡ሰገል።በመስቀልከ፡ወበሰይፈ፡መዓትከ፡ሠርዎሙ፡ለፀረ፡መስቀልከ።ወእለ፡ይፈቅዱ፡ይገፍትኡ፡ወንጌለ፡መለኮትከ፡ይኩነ፡ግፍቱዓነ፡እምገጸ፡ምድር”።ትርጉም፦ለክቡር፡መስቀል፡የተሰጠው፡የጸጋ፡ሀብት፡እንደምን፡የሚያህል፡ነው!መስቀልህ፡በውጊያ፡ጊዜ፡የጦር፡መሣርያ፣ለወታደሮችህም፡የመለኮት፡ሰይፍ፡ነው፤መስቀልህ፡በጠብ፡ጊዜ፡ማዕከሉን፡የሚመታ፣ኃጢአትንም፡ግንብ፡የሚያፈርስ፡ነው፤መስቀል፡ለሙት፡ልጆች፡አባት፡ለባልቴቶችም፡ዳኛ፡ነው፤መስቀልህ፡በባሕር፡ለሚጨነቁ፡ጸጥ፡የሚያደርግ፣በምድረ፡በዳ፡ለሚከራተቱም፡ወደብ፡ነው፤መስቀልህ፡ለዕውራን፡መሪ፤ለአንካሶችም፡ምርኩዝ፣ለድኩማንም፡ኃይላቸው፡ነው፤መስቀልህ፡ሕፃናት፡ምእመናንን፡በቤተ፡ክረስቲያን፡ጡቶች፡የሚያሳድግ፡ዕፅ፡ነው፤መስቀልህ፡ለነገሥታት፡አክሊል፡ነው፤መስቀልህ፡ለክርስቶሳውያን፡ትምክህታቸው፡ነው፤መስቀልህ፡ጠንቋዮችን፡የሚያጠፋ፣እናውቃለን፡ባዮችንም፡የሚበትን፡ነው፤መስቀልህ፡የካህናት፡ሰያሚያቸው፣የዲያቆናትም፡የተልዕኳቸው፡ሽልማት፡ነው፤መስቀልህ፡የወደቁትን፡የሚያነሣቸው፣ደካሞችንም፡እንደ፡ዋልያ፡የሚያሮጣቸው፡ነው፤መስቀልህ፡ለሙሽራህ፡ለቤተ፡ክርስቲያን፡ጥሎሿ፣በምኩራብ፡ለፈታሃትም፡ምልክቷ፡ነው፤መስቀልህ፡በእርሱ፡ለሚታመኑ፡የእምነት፡መሠረት፣የሃይማኖትም፡ዓምድ፡ነው፤መስቀልህ፡ጥንቆላን፡ሁሉ፡ማርከሻ፣መተትንም፡ሁሉ፡ማጥፊያ፡ነው፤በመስቀልህና፡በቁጣህ፡ሰይፍ፡የመስቀልህን፡ጠላቶች፡በትናቸው፤የመለኮትህንም፡ወንጌል፡ሊያጠፋ፡የሚፈልጉ፡ሁሉ፡ከምድር፡ገጽ፡የጠፋ፡ይሁኑ።አባ፡ጊ­ዮርጊስ፡ዘጋሥጫ፡በውዳሴ፡መስቀል፡­ላይ4፥61። *የዕለቱ፡ምልጣን፡ግእዝ፦”ይቤሎሙ፡ኢየሱስ፡ለአይሁድ፡እመኑ፡ብየ፡ወእመኑ፡በአቡየ፡ዮምሰ፡ለእሊዓየ፡አበርህ፡በመስቀልየ”።ትርጉም፦ኢየሱስ፡አይሁድን፡በእኔ፡እመኑ፡በአባቴም፡እመኑ፡ዛሬ፡ለወዳጆቼ፡በመስቀሌ፡አበራለሁ፡፡ *የዕለቱ፡ዓራራይ፡ዜና፦”መስቀል፡ብርሃን፡ለኲሉ፡ዓለም፡መሠረተ፡ቤተክርስቲያን፡በከመ፡ይቤ፡ዳዊት፡በመዝሙር፡ሐነጸ፡መቅደሶ፡በአርያም”።ትርጉም፦መስቀል፡ብርሃን፡ነው፤ለዓለም፡ሁሉ፡የቤተክርስቲያን፡መሰረነው።ዳዊት፡በመዝሙር፡በአርያም፡ማደሪያውን፡ስራ፡እንዳለ፡፡ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወረከብናሁ፡ውስተ፡ኦመ፡ገዳም።ንበውዕ፡እንከሰ፡ውስተ፡አብያቲሁ፡ለእግዚአብሔር።ወንሰግድ፡ውስተ፡መካን፡ኀበ፡ቆመ፡እግረ፡እግዚእነ።”መዝ131፥6-7፡ወይ­ም፡መዝ59፥4-5፡።የሚነበው፡ወ­ንጌል፡ዮሐ19፥25-28ወይም፡ማቴ­8፥16-28።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡­ዮሐንስ፡አፈወርቅ፡ቅዳሴ፡ነው።መል­ካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።         *ዛሬ፡መስከረም16፡ቀን *እንኳን፡ከጌታችን፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡መቃብር፡ላይ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ለታነፀችበትና፡ለተቀደሰችበት፡በዓል፣በኢየሩሳሌም፡አገር፡ንግሥት፡ዕሌኒ፡የገለጠቻቸው፡የከበሩ፡ቦታዎች፡ሁሉ፡ለተሠሩበትና፡ለከበሩበት፡በዓል(ለደመራ፡በዓል)፣በፋርስ፡ንጉሥ፡አሜኔሶር፡እጅ፡ተማርኮ፡ወደ፡ነነዌ፡አገር፡ለተወሰደ፡ከንፍታሌም፡ነገድ፡ለሆነ፡ለገባኤል፡ልጅ፡ለቅዱስ፡ጦቢት፡የዕረፍት፡በዓልና፡ተርታ፡ነገርንም፡እንዳይናገር፡ደንጊያ፡ጎርሶ፡ለኖረ፡ለታላቁ፡አባት፡ለአባ፡አጋቶን፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከቅዱሳን፡ከወርቅላ፣ከስምዖን፣ከመርቄኖስ፣ከሐሊ፡ከሮቂኖስ፣ከሉክያኖስ፣ከአርዝማኖስ፣ከጴጥሮስ፡ከሐና፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *አባ፡አጋቶን፦ወደ፡ቲቤያድ፡ገዳም፡ሲመጣ፡ገና፡ሕፃን፡ነበር።ያሳደገው፡ያስተማረው፡አባ፡ጴማን፡ነው።በመቀጠልም፡ወደ፡አስቄጥስ፡ተጉዞ፡ከአባ፡እስክድር፡እና፡ዞይለስ፡ጋር፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ኖሯል።ገዳመ፡አስቄጥስ፡ለመጀመርያ፡ጊዜ፡ሲጠፋ፡አባ፡አጋቶን፡ከደቀ፡መዝሙሩ፡ከአባ፡አብርሃም፡ጋር፡በመሆን፡ከደብረ፡ትሮኤ፡ሳይርቅ፡ከዓባይ፡ወንዝ፡አጠገብ፡መኖር፡ጀመረ። *አንድ፡ጊዜ፡ስለ፡አባ፡አጋቶን፡ትኅትና፡የሰሙ፡መነኰሳት፡ሊያዩት፡መጡ።የቁጣ፡ስሜቱን፡ወተውንና፡አለመተውን፡ለማረጋገጥ፡ብለው”አመንዝራውና፡ትዕቢተኛው፡አጋቶን፡ማለት፡አንተ፡ነህ?”አሉት።አባ፡አጋቶንም”አዎ፡ትክክል፡ነው”፡አላቸው።ቀጥለውም”ፍሬ፡የሌለው፡ነገር፡ዘወትር፡የምታወራ፡አጋቶን፡ማለት፡አንተ፡ነህ?”አሉት”አዎ፡ነኝ፡አላቸው።”መናፍቅ፡አጋቶን፡ማለት፡አንተ፡አይደለህምን?”ሲሉ፡ጠየቁት፡ያን፡ጊዜ፡ግን”መናፍቅስ፡አይደለሁም”ሲል፡መለሰላቸው።በዚህ፡ጊዜ”እስካሁን፡የተናገርንብህን፡ሁሉ፡ተቀብለህ፡የመጨረሻውን፡ለምን፡ተቃወምክ?”አሉት።አባ፡አጋቶንም”የመጀመሪያያዎቹን፡ወቀሳዎች፡ለነፍሴ፡ተስማሚዎች፡ናቸውና፡ተቀበልኳቸው።ኑፋቄ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡መለየት፡ነው፡እናም፡እኔ፡ከፈጣርዬ፡መለየት፡አልፈልግም፡አላቸው”።በዚህ፡የተነሣም፡የርሱ፡ሕይወት፡አስደነቃቸው። አንድ፡ቀን፡አባ፡አጋቶን፡በእጁ፡የሠራቸውን፡ነገሮች፡ለመሸጥ፡ወደ፡ገበያ፡ሲወጣ፡በመንገድ፡ዳር፡አንድ፡ሽባ፡ሰው፡አገኘ።ሽባውም፡የት፡እንደሚሄድ፡አባ፡አጋቶንን፡ጠየቀው።”አንዳንድ፡ነገሮች፡ለመሸጥ፡ወደ፡ገበያ፡እሔዳለው”አለው።ሽባው፡ሰውም”እባክህ፡ተሸከምህ፡ወደዚያ፡ውሰደኝ”ሲል፡ለመነው።አባ፡አጋቶንም፡ያንን፡ሰው፡ተሸክሞ፡ወደ፡ከተማ፡ወሰደው።ሽባው፡ሸውዬ”ዕቃዎችን፡ከምትሸጥበት፡ቦታ፡አጠገብ፡አኑረኝ”፡አለው።አባ፡አጋቶንም፡እንደዚያው፡አደረገው።አባ፡አጋቶን፡የመጀመርያውን፡ዕቃ፡ሲሸጥ”ምን፡ያህል፡ሸጥከው?”ብሎ፡ሽባው፡ሰው፡ጠየቀው።እርሱም፡ዋጋውን፡ነገረው።ያም፡ሽባ፡ሰው”እባክህ፡ዳቦ፡ግዛልኝ”ሲል፡ለመነውና፡ገዛለት።አባ፡አጋቶን፡ሁለተኛው፡ዕቃ፡ሲሸጥ”ምን፡ያህል፡ሸጥከው”ሲል፡ያሰው፡ጠየቀው።እርሱም፡ዋጋው፡ነገረው”እባክህ፡ይህን፡ነገር፡ግዛልኝ”ሲል፡ለመነው።አባ፡አጋቶንም፡ገዛለት።በዚህም፡መልኩ፡ሁሉንም፡ዕቃዎች፡ሸጦ፡በጨረሰ፡ጊዜ፡ያሽባ፡ሰው፡ወደ፡በዓትህ፡ትመለሳለህን?”ሲል፡ጠየቀው”አዎ”እንግደውስ፡እባክ፡ቀድሞ፡ወደአገኸኝ፡ስፋራ፡አዝለህ፡መልሰኝ”፡አለው።አባ፡አጋቶንም፡ያን፡ሽባ፡ሰው፡ተሸክሞ፡ወደ፡ቀድሞ፡ቦታው፡መለሰው።በዚህ፡ጊዜ፡ሽባው፡ሰው”አባ፡አጋቶን፡በሰማይና፡በምድር፡በረከት፡ተሞላህ”ብሎ፡ተናገረው።ወድያው፡አባ፡አጋቶን፡አይኑን፡አንስቶ፡ሽባው፡ቢያየው፡በቦታው፡የለም።ሊፈትነው፡ይህን፡ያደረገው፡መልአከ፡እግዚአብሔር፡ነበር።ምንጭ፦በበረሐው፡ጉያ፡ውስጥ፡ከሚለው፡መጽሐፍ፡ዲያቆን፡ዳንኤል፡ክብረት፡ከጻፈው። *”ሰላም፡ለጦቢት፡መፍቀሬ፡ምጽዋት፡ዘተብህለ።እስመ፡ይገብር፡ምጽዋተ፡ወብዙኀ፡ሣህለ።እንዘ፡ምስለ፡ሕዝቡ፡ይሄሉ፡ሀገረ፡ነነዌ፡ማዕከለ።እምከመ፡ረከበ፡በእሴ፡ቅቱለ።እንበለ፡ይትብሮ፡ኢይጥዕም፡እከለ።”አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም16። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”እቤ፡አዐቅብ፡አፉየ፡ከመ፡ኢይስሐት፡በልሳንየ።ወአንቀርኩ፡ዐቃቤ፡ለአፋየ።ሶበ፡ይትቃወሙኒ፡ኀጥአን፡ቅድሜየ”።መዝ38፥1፡ወይም፡መዝ50፥18-19።የሚነበበው፡ወንጌል9፥1-12፡ወይም፡ዮሐ10፥22-42።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡ቅዳሴ፡እግዚእነ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

   *”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።          *ዛሬ፡መስከረም15፡ቀን *እንኳን፡ለኢትዮያዊው፡ጻድቅ፡ማኅሌተ፡ጽጌ፡ከአባ፡ጽጌ፡ድንግል፡ጋር፡በአንድነት፡እንደ፡አንድ፡ልብ መካሪ፡እንደ፡አንድ፡ቃል፡ተናጋሪ፡በመሆን፡ለደረሱት፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡ገብረ፡ማርያም፡ዘደብረ፡ሐንታ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለዲያቆናት፡አለቃ፡ለቀዳሜ፡ሰማዕት፡ለቅዱስ፡እስጢፋኖስ፡ለሥጋው፡ፍልሰት፡ለመታሰብያ፡ቀን፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ጠራው፡ከሚባል፡አገር፡እግራቸው፡በውኃው፡ሳይርስ፡በእግራቸው፡በባሕር፡ላይ፡ሲራመዱ፡ከነበሩት፡ከከበረ፡ፃድቅ፡ከአባ፡ጴጥሮስ፡በዓለ፡ዕረፍት፡ረድኤት፡በረከት፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለፍልሰተ፡ሥጋከ፡ዘተረክበ፡እምተከብቶ።አመ፡፲ወ፭፡ለወርኅ፡መስከረም፡ቲቶ።ተወኪፈከ፡እስጢፋኖስ፡መሥዋዕተ፡ሰላምየ፡በኢያስትቶ።ምስሌየ፡ግበር፡እግዚኦ፡ለሠናይቲከ፡ትእምርቶ።ናሁ፡ለውዳሴከ፡ርኢኩ፡ማኅለቅቆ”።ትርጉም፡ቅዱስ፡እስጢፋኖስ፡ሆይ!ቲቶ፡በሚባል፡መስከረም15፡ቀን፡ከተቀበረበት፡ለተገኘ፡ለሥጋህ፡ፍልሰት፡ሰላምታ፡ይገባል።ጌታዬ፡ባለማቃለልም፡የሰላሜን፡መሥዋዕት፡ተቀብለህ፡የበጎነትህን፡ምልክት፡ከእኔ፡ጋር፡አድርግ።የምስጋናህንም፡ፍጻሜ፡እነሆ፡አይቻለሁ።መልክአ፡ቅዱስ፡እስጢፋኖስ። *”ሰላም፡እብል፡ለጴጥሮስ፡ብሕትወ።ኮከበ፡ጠራው።ወውስተ፡ዓለም፡ኅሩም፡እምበሊዐ፡ኅብስት፡ወጼው።እስከ፡አስተርአየ፡በአምሳለ፡ምትሐት፡ሕስው።ተሴስዮ፡ሣዕር፡አብደረ፡በበድው”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም15። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ብፁዕ፡ዘኀረይኮ፡ወዘተወከፍኮ።ወዘአኀደርኮ፡ውስተ፡አዕፃዲከ።ጸገብነ፡እግዚኦ፡እምበረከተ፡ቤትከ”።መዝ64፥4።የሚነበበው፡ወንጌል፡ሉቃ10፥30-38።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Continue reading

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።           *ዛሬ፡መስከረም14፡ቀን *እንኳን፡ለኢትዮጽያውያን፡ጻድቃን፡ለቀዳማዊው፡ንጉሥ፡ለዓምደ፡ጽዮን፡ልጅ፡ለነበሩና፡ድንጋዩን፡እንደ፡ጀልባ፡ተጠቅመው፡የጣናን፡ሐይቅ፡ለተሻገሩት፡ለታላቁ፡አባት፡አቡነ፡ያሳይ፡ዘማንዳባና፡እጆቻቸው፡እንደፋና፡እያበሩ፡ለጣና፡ሐይቅ፡ገዳማት፡በመብራትነት፡ያገለግሉ፡ለነበሩት፡ለፃህና፡መምህራን፡ለሆኑ፡አባቶች፡ዐሥራ፡አንደኛ፡ለሆነ፡ለፃና፡መምህር፡ለቅዱስ፡አባት፡ለአቡነ፡ጴጥሮስ፡ቀዳማዊ፡ለዕረፍታቸው፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ሃምሳ፡ዓመት፡በዓምድ፡ላይ፡ቆሞ፡ሲጸልይ፡ከኖረው፡አቡነ፡አጋቶን፡ዘአምድ፡ከዕረፍቱ፡በዓል፣ከቀሲስ፡ዴግና፡ዕረፍት፣ከሰማዕት፡መቃራ፣ከበርተሎሜዎስ፡ከአውዳራና፡ከናሶን፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *አቡነ፡ጴጥሮስ፡ቀዳማዊ፡-ትውልድ፡ሀገራቸው፡ሸዋ፡ቡልጋ፡ልዩ፡ስሙ፡ደብረ፡ጽላልሽ፡ነው፡፡ጻድቁ፡በዐፄ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ዘመን፡ለ48፡ዓመታት፡የቅዱስ፡ገላውዲዮስን፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ሲያጥኑ፡ኖረዋል፡፡ከተሰዓቱ፡ቅዱሳን፡አንዱ፡የሆኑት፡አቡነ፡ሊቃኖስ፡እጆቻቸው፡እያበሩ፡ለገዳሙ፡መብራትነት፡ይጠቀሙባቸው፡እንደነበረው፡ሁሉ፡የአቡነ፡ጴጥሮስ ቀዳማዊም፡እጆቻቸው፡እንደፋና፡እያበራ፡ለጣና፡ሐይቅ፡ገዳማት፡በመብራትነት፡ያገለግል፡ነበር፡፡ጻድቁ፡ለ31፡ዓመታት፡ከመላእክት፡ጋር፡እየተነጋገሩ፡የኖሩ፡ሲሆን፡መናም፡ከሰማይ፡እያወረዱ፡መነኮሳቱን፡ይመግቡ፡ነበር፡፡ድውያንን፡በመፈወስ፣ ሙታንን፡በመንሣት፡ብዙ፡አስተደናቂ፡ተአምራት፡እያደረጉ፡ወንጌልን፡በሀገራችን፡ዞረው፡በማስተማር፡እግዚብሔርን፡ሲያገለግሉ፡ኖረው፡በዚህች፡ዕለት፡በሰላም፡ዐርፈው፡ቅድስት፡ነፍሳቸውን፡ቅዱሳን፡መላእክት፡በክብር፡ተቀብለዋታል፡፡ምንጭ፡መዝገበ፡ቅዱሳንና፡ስንክሳር። *”ሰላም፡ለአጋቶን፡አክሊለ፡ወሞገሳ።ሀገረ፡ተንሳ።በብዙኅ፡ጻሕቅ፡ለመግሥተ፡ሰማይ፡እንዘ፡የኃሥሣ።፡ፃመወ፡ዓመታተ፡እስራ፡ወሠላሳ።ወበላዕለ፡ዓምድ፡አዝማናተ፡ኃምሳ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም14። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወወሀብኮሙ፡ትእምርተ፡ለእለ፡ይፈርሁከ።ከመ፡ያምሥጡ፡እምገጸ፡ቅስት።ወይድኀኑ፡ፍቁራኒከ”።መዝ59፥9-10።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ14፥22-36።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Continue reading

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።           *ዛሬ፡መስከረም13፡ቀን *እንኳን፡ለታላቁና፡ቅዱስ፡የሆነ፡የቂሣርያ፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡ቅዱስ፡ባስልዮስ፡ላደረገው፡ተአምር፡ለመታሰቢያ፡በዓል(አንድ፡ጎልማሳ፡አገርልጋይ፡የጌታውን፡ልጅ፡ስወደዳት፡እርሷንም፡ከመውደዱ፡የተነሣ፡እርሷን፡ለማግባት፡ብሎ፡ወደ፡አንድ፡ከሀዲ፡ሥራየኛ፡ሔዶ፡እግዚአብሔር፡ክዶ፡በሰይጣን፡አምኖ፡በእጁ፡ፈርሞ፡ለሰይጣን፡ሰጠው፡ይህንን፡የጽሕፈት፡ደብዳቤ፡በእግዚአብሔር፡ኃይልና፡በጸሎቱ፡ቅዱስ፡ባስልዮስ፡በመደምሰስ፡ድንቅ፡ተአምር፡ያደረገበት፡ቀን)በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰበው፦ከከበረ፡ከባሕታዊ፡ከአባ፡ይስሐቅ፡ከመታሰቢያው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።  *”በዛቲ፡ዕለት፡እግዚአብሔር፡ገብረ።በእደ፡ባስልዮስ፡መንክረ።በአፍቅሮ፡ወለት፡አሐቲ፡ኀበ፡መሠርይ፡ዘሖረ።እንዘ፡ይከሥት፡በቅድመ፡ሕዝብ፡መጽሐፈ፡ክህደቱ፡ሥውረ።እምእደ፡ሰይጣን፡አንገፈ፡ወፄወወ፡ገብረ።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም13። *መዝሙር ዘሰንበት(የዚህ፡ሳምንት፡መዝሙር)በ፭:እኩት፡አንተ፡ወስቡሕ፡ስምከ፡ወዓቢይ፡ኃይልከ፤ዘተዓርፍ፡በአርያም፡ወትሴባሕ፡በትሑታን፤ዘአንተ፡ሠራዕከ፡ሰንበተ፡ለዕረፍት፡ወወሀብከ፡ሲሳየ፡ዘበጽድቅ፡ለኲሉ፡እግዚኦ፡ባርክ፡ፍሬሃ፡ለምድር፤መሐሪ፡ወጻድቅ፡መኑ፡ከማከ፤ዘታርኁ፡ክረምተ፡በጸጋከ፡ነፍስ፡ድኅንት፡ወነፍስ፡ርኅብት፤እንተ፡ጸግበት፡ተአኲተከ።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ምድርኒ፡ወሀበት(ትሁብ)ፍሬሃ።ወይባርከነ፡እግዚአብሔር፡አምላክነ።ወይባርከነ፡እግዚአብሔር”።መዝ66፥6-7።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማር4፥24-39።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Continue reading

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”። *ዛሬ፡መስከረም12፡ቀን *እንኳን፡ለሊቀ፡መላእክት፡ለቅዱስ፡ሚካኤል፡እግዚአብሔር፡ወደ፡አሞፅ፡ልጅ፡ወደ፡ነቢዩ፡ኢሳይያስ፡ለንጉሱ፡ሕዝቅያስ፡ከደዌው፡እንዳዳነው፡በእድሜው፡ላይ፡አስራ፡አምስት፡አመት፡እንደተጨመረለት፡ንገረው፡ብሎ፡ለተላከበት፡ለወራዊ፡መታሰብያ፡በዓልና፡በኤፌሶን፡ሀገር፡በ431ዓ.ም(ሦስተኛው፡ጉባኤ)ሁለት፡መቶ፡ኤጲስ፡ቆጶሳት፡ንስጥሮስን፡ለማውገዝ፡ለተሰበሰቡበት፡ቀን፡ለመታሰቢያ፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከሰማዕት፡አፍላሆስ፡ከመታሰቢያውና፡ከሥጋው፡ፍልሰት፣ከእስክድርያ፡አገር፡ከሆኑ፡ከባልንጀሮቹ፡ሰማዕታትም፡ከመታሰቢያቸው፣ከሰማዕታት፡ከሉዩራስና፡ባሌኒኮስ፣ከቅዱስ፡ኢያቄምና፡ከቅድስት፡ሐናም፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለ፪፻፡ኤጲስ፡ቆጶሳት፡እለ፡ተጋብኡ፡በኤፌሶን፡ሀገር፤ወአጽንኡ፡ሃይማኖተ፡በእግዚአብሔር”።ትርጉም፦በኤፌሶን፡ሀገር፡ተሰብስበው፡ሃይማኖትን፡በእግዚአብሔር፡የጸኑ፡ለኾኑ፡ለኹለት፡መቶው፡ኤጲስ፡ቆጶሳት፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *”ሰላም፡ለክሙ፡ሐራ፡ክረስቶስ፡መድኅን።ጥዑማነ፡ዜና፡ወዝክር፡እምአስካለ፡ወይን።ርእሰ፡ንስጥሮስ፡ትምትሩ፡በሰይፈ፡ሃይማኖት፡ርሱን።ዘተጋባእክሙ፡ሀገረ፡ኤፌሶን።ክልኤቱ፡ምዕት፡ጳጳሳት፡ኄራን”።ትርጉም፦በጋለ፡የሃይማኖት፡ሰይፍ፡የንስጥሮስን፡ራስ፡ትቆርጡ፡ዘንድ፡በኤፌሶን፡ሀገር፡የተሰበሰባችኊ፡የኾናችኊ፡ደጋጎች(የተመረጣችሁ)ኹለት፡መቶ፡ሊቃውንት፡ዜናችኹና፡መታሰቢያችኊ፡ከወይን፡ፍሬ፡ይልቅ፡የጣፈጠ፡የመድኅን፡ክርስቶስ፡ጭፍራ፡ሰላምታ፡ለእናንተ፡ይገባል። *”ሰላም፡ለምቅወምከ፡ዘልዑል፡ማዕረጋ።እምቅዋመ፡አእላፍ፡እንግልጋ።ሚካኤል፡መንፈስ፡ዘንበለ፡ሥጋ።ታድኅን፡ዘተመንደበ፡ለማዕበለ፡ባሕር፡እምጹጋ፡ወለእለ፡በበድው፡ትባልሕ፡በጸጋ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም12። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ይትዐየን፡መልአከ፡እግዚአብሔር፡ዐውዶሙ።ለእለ፡ይፈርህዎ፡ወያድኅኖሙ።ጠዐሙ፡ወታእሙሩ፡ከመ፡ኄር፡እግዚአብሔር።”መዝ33፥7-8።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ18፥15-19።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ቄርሎስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።    *እንኳን፡ለአንጾኪያ፡ነገሥታት፡አባታቸውና፡መካሪያቸው፡ለሆነ፡በዲዮቅልጥያኖስ፡ዘመን፡ለነበረውና፡ጌታችን፡ከሞት፡እያስነሣው፡በጽኑ፡ሥቃይና፡ተጋድሎ፡ሲጋደል፡ለኖረው፡ለታላቁ፡ሰማዕት፡ለቅዱስ፡ፋሲለደስና፡በቅዱሳን፡አባቶቻችን፡ሐዋርያት፡ዘመን፡እግዚአብሔርን፡ያገለገለ፡የጭፍራ፡አለቃ(፻አለቃ)፡ለሆነ፡ትሩፋቱና፡ገድሉም፡ላማረ፡ለጻድቁ፡ሰው፡ለቅዱስ፡ቆርኔሌዎስ፡የዕረፍታቸው፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን፡፡በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦የስሟ፡ትርጓሜ፡ጣፋጭ፡ከሆነ፡ከከበረች፡ከሰማዕቷ፡ከቅድስት፡በነፍዝዝ፡የዕረፍት፡በዓል፣ስማቸው፡ሱርስ፣አጤኬዎስና፡መስተሐድራ፡ከሚባሉ፡ሦስት፡ገበሬዎች፡ከእስና፡አገር፡ሰዎች፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፣ከእስክድርያ፡አገር፡በንጉሥ፡ዘይኑን፡ዘመን፡ከነበረች፡ከቅድስት፡ታዖድራ፡ዕረፍት፣ከቅዱሳን፡ከባስልዮስ፡ሰማዕትና፡ከኢየሩሳሌም፡ኤጲስቆጶስ፡ከቴዎድሮስ፡ከሰማዕት፡አለቃ፡ከቀውስጦስም፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለፋሲለደስ፡እምነ፡ክሣዱ፡ዘአንጠብጠበ።ደመ፡ቀይሐ፡ወጸዓድዒደ፡ሐሊበ።ምስለ፡አዝማዲሁ፡ወሰብኡ፡እስመ፡ለሞት፡ተውህበ።በከመ፡ኮኖሙ፡ዲበ፡ምድር፡አበ።ዘበሰማያት፡ተሠይመ፡አቡሆሙ፡ካዕበ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም11። *የዕለቱ፡አንገርጋሪ፡ግእዝ፡ዜማ፦ሃሌ፡ሉያ”በዛቲ፡ዕለት፡ይሴብሑከ፡መላእክት፡እለ፡ተጋብኡ፡ውስተ፡ዝንቱ፡ቤት፡ፋሲለደስ፡ሰማዕት፡ዘነገሥከ፡በሰማያት፡አማን፡ምዑዝ፡ከመ፡እፍረት።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወይርአ­ዩ፡አሕዛብ፡በቅድመ፡አዕይንቲነ።በ­ቀለ፡ደሞሙ፡ለአግብርቲከ፡ዘተክዕወ።ይባዕ፡ቅድሜከ፡ገዐሮሙ፡ለሙቁሓን”።መዝ78፥10-11።የሚነበበው፡­ወንጌል፡ሉቃ21፥12-21።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ባስልዮስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

ዛሬ፡መስከረም10፡ቀን

“በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”። *እንኳን፡ለእመቤታች፡ለቅድስት፡ድንግል፡ማርያም፡በፄዴንያ፡አገር፡በማርታ፡ቤት፡ሥጋ፡የለበሠች፡ከምትመስል፡ከእመቤታች፡ሥዕል፡ከሠሌዳዋ፡ቅባት፡እየተንጠፈጠፈ፡ተአምር፡ለሠራችበት፡ቀን፡መታሰብያ፡በዓልና፡የጌታችን፡የአምላካችን፡የመድኃኒታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡­ቅዱስ፡መስቀል፡ወደ፡አገራችን፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ለገባበት(ተቀጽል፡ጽጌ)አፄ፡መስቀል)ቀን፡ለመታሰቢያ፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪም፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦አምላክን፡የወለደች፡የእመቤታችን፡የቅድስት፡ድንግል፡ማርያም፡የተወለደችበት፡ነው፡የሚሉ፡አሉ።(ይህም፡የአስቄጥስ፡ገዳም፡የከበረ፡አባ፡መቃርስ፡በጻፈው፡መጽሐፈ፡ግጻዌ፡ተጽፎል፡እንዲሁም፡ደግሞ፡በላዕላይ፡ግብጽ፡በሚገኝ፡መጽሐፈ፡ግጻዌ፡የከበረች፡ድንግል፡እመቤታችን፡የከበረች፡ሐና፡በታኅሣሥ፡ወር፡በዐሥራ፡ሰባት፡እንደፀነሰቻትና፡መስከም፡በዐሥር፡ቀን፡እንደወለደቻት፡ተጽፍአል)፣ከከሀዲው፡ሆሎፎርኒስ፡እጅ፡በጥበቧ፡እስራኤልን፡ካዳነቻቸው፡ከጥበበኛ፡ከከበረች፡ከዮዲት፡በዓለ፡ዕረፍትና፡ከከበረች፡ሰማዕት፡ቅድስት፡መጥሮንያ፡ዕረፍት፣ከቅድስት፡አትናስያና፡ሦስት፡ልጆቿ፡ከመታሰቢያቸው፡በረከትና፡ረድኤትን፡ያሳትፈን። “መስቀል፡­ጒድበ፡ሙስና፡ዲበ፡ሰይጣን፡ወሰይፈ­፡ሙቃየ፡አርእስቲሆሙ፡ለአጋንንት፤መስቀል፡ረምኃ፡እሳት፡ዘይረግዞሙ፡ለመናፍስት፡ርኵሳን፤ወሐፀ፡መብረቅ፡ዘይደጒፆሙ፡ለሠራዊተ፡መስቴማ።መስቀል፡ፀወን፡ዘኢይክል፡በጺሐ፡ኀቤሁ፡ዘኢነሥአ፡ማኅተመ፡ሥላሴ።መስቀል፡ወልታ፡ጽድቅ፡ዘእምየማን፡ወእም፡ጸጋም።መስቀል፡ንዋየ፡ሐቅል፡ለፀብዕ፡በከመ፡ይቤ፡ጳውሎስ፡ሐዋርያ፡እስመ፡ቀትልክሙ፡ኢኮነ፡ምስለ፡ዘሥጋ፡ወደም።መስቀል፡ጽርዐ፡ሃይማኖት፡ዘኢይክል፡ሰጢጦቶ፡ሥጽረተ፡ሐፀ፡ወኢደርብዮቶ፡ኵያንው፡ወአርማኅ።መስቀል፡ዘገብረ፡በአምሳሊሁ፡ለእደ፡ሙሴ፡በገዳም፡ራፊድ፡በእንተ፡ፀብዐ፡አማሌቅ።መስቀል፡ዘአጥዐሞ፡ለማይ፡መሪር፡በገዳም፡ሱር፡ሶበ፡ተወድየ፡ውስቴቱ፡በእደ፡ሙሴ።መስቀል፡ማኅተመ፡ቅድስና፡ወንጽሕ።መስቀል፡አክሊለ፡መዊዕ፡ዘመስተጋድላን፡ወሠርጎ፡ትርሲት፡ለእለ፡ተዓሥሩ፡ውስተ፡መርዐ፡በግዑ።መስቀል፡ነቅዕ፡ዘኢይነጽፍ፡ወአዘቅተ፡ክብር፡ዘምሉዕ፡ረባሐ”።­ትርጉም፦መስቀል፡ሰይጣንን፡የሚያ­ጠፋ፡ምሳር፡ነው፤የአጋንንትንም፡ራ­ሶች፡የሚቆርጥ፡ሰይፍ፡ነው፤መስቀል፡ርኩሳን፡መናፍስትን፡የሚወጋቸው፡የእሳት፡ዘገር፡ነው፤የአመስቴማውያንንም(የጠላት፣የከሳሽ፡የጠበኛ)ሠራዊት፡የሚመታ፡የመብረቅ፡ጦር፡ነው።መስቀል፡ማኅተመ፡ሥላሴ(የሥላሴ፡ልጅነት)የሌለው፡ሰው፡ወደእርሱ፡ሊቀርበው፡የማይቻለው፡አምባ፡መጠጊያ፡ነው።መስቀል፡ከግራ፡ከቀኝም፡ለሚመጣ(ጠላት)የጽድቅ፡ጋሻ፡ነው።ጳውሎስ”ውጊያችሁ፡ከሥጋና፡ከደም፡ጋር፡አይደለም”እንዳለው፡መስቀል፡የጦር፡መሣርያ፡ነው።መስቀል፡የጦር፡ውጋት፡ሊቀድደው፤የቀስትና፡የዘንግም፡ጫፍ፡ሊበሳው፡የማይችል፡የሃይማኖት፡ጥሩር፡ነው።መስቀል፡አማሌቃውያንን፡ለመውጋት፡በራፊድ፡በረሐ፡በዘረጋው፡በሙሴ፡እጅ፡አምሳል፡የተሠራ፡ነው።መስቀል፡በሙሴ፡እጅ፡ወደ፡ውስጥ፡በተጨመረ፡ጊዜ፡መራራውን፡ውኃ፡በሱር፡በረሐ፡ያጣፈጠ፡ነው።መስቀል፡የቅድስናና፡የንጽሕና፡ማኅተም፡ነው።መስቀል፡ለሚጋደሉ፡የድል፡አክሊል፤ወደ፡በጉ፡ሰርግ፡ለተጠሩትም፡የሰርግ፡ልብሳቸው፡ነው።መስቀል፡የማይነጥፍ፡ምንጭ፤በቁዔትም(ጥቅምም)፡የሞላበት፡የክብር፡ጉድጓድ፡ነው።አባ፡ጊ­ዮርጊስ፡ዘጋሥጫ፡በውዳሴ፡መስቀል፡­ላይ1፥3። “ሰላም፡ለሥዕልኪ፡ሀፈ፡ማኅየዌ።በፄዴንያ፡ወኢትዮጵያ፡በአውኀዘት፡በኢሕሳዌ።ለመፀብሐዊ፡ማቴዎስ፡ማርያም፡እንተ፡ረሰይኪዮ፡ወንጌላዌ።ይኩነነ፡ወትረ፡ፀሎትኪ፡እምዘመነ፡ኵሉ፡ምንሳዌ።ዓቃቤ፡ዘመዓልት፡ወዘሌሊት፡ሀላዌ”።መልክአ፡ሥዕል። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወትቀውም፡ንግሥት፡በየማንከ።በአልባሰ፡ወርቅ፡ዑፅፍት፡ወኁብርት።ስምዒ፡ወለትየ፡ወርእዪ፡ወአፅምዒ፡እዝነኪ።”መዝ44፥9-10።የሚነበበው፡ወንጌል፡ሉቃ1፥46-57፡ወይም፡ማቴ25፥1-14።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የእመቤታች፡ማርያም፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንል።

Continue reading

*እንኳን፡በሮሜ፡አገር፡ፍሩምያ፡በምትባል፡ከተማ፡በመላእክት፡አለቃ፡በቅዱስ፡ሚካኤል፡በስሙ፡በተሰራ፡ቤተ፡ክረስቲያን፡ላደረገው፡ተአምር፡መታሰቢያ፡በዓልና፡ከኀላፊው፡ከዚህ፡ዓለም፡መንግሥቱ፡መንኖ፡ተጋድሎውን፡በዛፍ፡ላይ፡ሁኖ፡ለፈጸመ፤የደረቀውን፡ግንድ፡ላለመለ፣ለጽጌ፣ለፍሬ፡ለአደረሰ፡ላሳየ፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ላሰኘ፡ለንጉሥ፡ያሳይ፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦መጺል፡ከምትባል፡አገር፡ኤጲስቆጶስ፡ከቅዱስ፡አባት፡ከአባ፡ቢሶራ፡በሰማዕትነት፡ከዐረፈ፣ከቅዱስ፡ፋሲለደስ፡ጋር፡ዐሥራ፡አራት፡ሺህ፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ወንዶችና፡ሰባት፡ሴቶችም፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለአባ፡ያሳይ፡ብእሴ፡ሰማይ፤ለአምላኩ፡ቀናኢ፤ሐራይ፡መዋኢ”።ትርጉም፦ድል፡ነሺ፡ጭፍራ፡ለአምላኩ፡ቀናተኛ፡የሰማይ፡ሰው፡ለኾነ፡ለአባ፡ያሳይ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *”ሰላም፡ለያሳይ፡እምነ፡መንግሥቱ፡ዘተድህለ።መንግሥተ፡ሰማያት፡ያድምዕ፡ወዘኢየኀልፍ፡ብዕለ።ውስተ፡ጉንደ፡ዕፅ፡ይቡስ፡አመ፡ተለዓለ።በትሩፋቲሁ፡ከመ፡ያርኢ፡ኃይለ።አሥረፀ፡ሶቤሃ፡ወአወጽአ፡ቔጽለ”።ትርጉም፦የማያልፍ፡ሀብትንና፡መንግሥተ፡ሰማያትን፡ያገኘ፡ዘንድ፡ከምድራዊው፡መንግሥቱ፡የኰበለለ፡ለኾነ፡ለያሳይ፡ሰላምታ፡ይገባል፤በትሩፋቱ፡ኃይልን፡ያሳይ፡ዘንድ፡በደረቀ፡ዕንጨት፡ግንድ፡ላይ፡በወጣ፡ጊዜ፡በዚያን፡ጊዜ፡ቅጠሎችን፡አውጥቶ፡ለመለመ። *”ሰላም፡እብል፡ለዓቢይ፡መንክሩ።ዘተክሥተ፡ዮም፡በውስተ፡ዳቤሩ።ፈለገ፡ማይ፡ይሚጡ፡እንዘ፡ይመክሩ።ተሠጥቀ፡ኰኵሕ፡እንተ፡ዐላውያን፡አንበሩ።ሶበ፡ሚካኤል፡ዘበጦ፡በበትሩ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም9። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ደምፁ፡ወተሐምጉ፡ማያቲሆሙ።ወአድለቅለቁ፡አድባር፡እምኃይሉ።ፈለግ፡ዘይውኅዝ፡ያስተፌሥሕ፡ሀገር፡እግዚአብሔር”።መዝ45፥3-4።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ7፥24-29።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ያዕቆብ­፡ዘሥሩግ፡ነው።­መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን­።

Continue reading