ዛሬ፡መስከረም11፡ቀን (21 Sept 2018)

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።
  
*እንኳን፡ለአንጾኪያ፡ነገሥታት፡አባታቸውና፡መካሪያቸው፡ለሆነ፡በዲዮቅልጥያኖስ፡ዘመን፡ለነበረውና፡ጌታችን፡ከሞት፡እያስነሣው፡በጽኑ፡ሥቃይና፡ተጋድሎ፡ሲጋደል፡ለኖረው፡ለታላቁ፡ሰማዕት፡ለቅዱስ፡ፋሲለደስና፡በቅዱሳን፡አባቶቻችን፡ሐዋርያት፡ዘመን፡እግዚአብሔርን፡ያገለገለ፡የጭፍራ፡አለቃ(፻አለቃ)፡ለሆነ፡ትሩፋቱና፡ገድሉም፡ላማረ፡ለጻድቁ፡ሰው፡ለቅዱስ፡ቆርኔሌዎስ፡የዕረፍታቸው፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን፡፡በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦የስሟ፡ትርጓሜ፡ጣፋጭ፡ከሆነ፡ከከበረች፡ከሰማዕቷ፡ከቅድስት፡በነፍዝዝ፡የዕረፍት፡በዓል፣ስማቸው፡ሱርስ፣አጤኬዎስና፡መስተሐድራ፡ከሚባሉ፡ሦስት፡ገበሬዎች፡ከእስና፡አገር፡ሰዎች፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፣ከእስክድርያ፡አገር፡በንጉሥ፡ዘይኑን፡ዘመን፡ከነበረች፡ከቅድስት፡ታዖድራ፡ዕረፍት፣ከቅዱሳን፡ከባስልዮስ፡ሰማዕትና፡ከኢየሩሳሌም፡ኤጲስቆጶስ፡ከቴዎድሮስ፡ከሰማዕት፡አለቃ፡ከቀውስጦስም፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለፋሲለደስ፡እምነ፡ክሣዱ፡ዘአንጠብጠበ።ደመ፡ቀይሐ፡ወጸዓድዒደ፡ሐሊበ።ምስለ፡አዝማዲሁ፡ወሰብኡ፡እስመ፡ለሞት፡ተውህበ።በከመ፡ኮኖሙ፡ዲበ፡ምድር፡አበ።ዘበሰማያት፡ተሠይመ፡አቡሆሙ፡ካዕበ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም11።
*የዕለቱ፡አንገርጋሪ፡ግእዝ፡ዜማ፦ሃሌ፡ሉያ”በዛቲ፡ዕለት፡ይሴብሑከ፡መላእክት፡እለ፡ተጋብኡ፡ውስተ፡ዝንቱ፡ቤት፡ፋሲለደስ፡ሰማዕት፡ዘነገሥከ፡በሰማያት፡አማን፡ምዑዝ፡ከመ፡እፍረት።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወይርአ­ዩ፡አሕዛብ፡በቅድመ፡አዕይንቲነ።በ­ቀለ፡ደሞሙ፡ለአግብርቲከ፡ዘተክዕወ።ይባዕ፡ቅድሜከ፡ገዐሮሙ፡ለሙቁሓን”።መዝ78፥10-11።የሚነበበው፡­ወንጌል፡ሉቃ21፥12-21።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ባስልዮስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Comments are closed.