*እንኳን፡ለሊቀ፡መላእክት፡ለቅዱስ፡ሩፋኤል፡ለተሾመበት፣ጦቢትን፡አይኑን፡ለአበራለትና፡ልጁ፡ጦብያን፡ለረዳበት፣የራጉኤልን፡ልጅ፡ሣራን፡ተቆራኝቷት፡ከነበረው፡ከአስማንድዮስ፡ጋኔን፡ለአዳነበት፡በዓል፣ለሊቀ፡ካህን፡ለኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ምሳሌ፡ለሆነ፡ለካህኑ፡መልከፄዴቅ፡ለመታሰቢያ፡በዓሉና፡ለኢትዮጵያ፡ንጉስ፡መልካም፡ስም፡አጠራር፡ላለው፡ለአፄ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ለዕረፍቱ፡ቀን፡መታሰቢያ፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰበው፦ሰንዱን፡ከሚባል፡አገር፡ከቅዱስ፡ሰራጵዮን፡ዕረፍት፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን፡። “ሰላም፡ለአፃብኢከ፡አዕይንተ፡ጦቢት፡ዘፈሳ።ወለአፅሪከ፡ደርገ፡ዘኵሕላ፡ሐሞት፡ዓሣ።መልአከ፡ምሥጢር፡ሩፋኤል፡ወዘውገ፡ርቡዓን፡እንስሳ።አዕይንትየ፡እግዚኦ፡አፃአብከ፡ይግሥሣ።ከመ፡እደ፡መልአክ፡ገስሳ፡ለነቢይ፡ዘሱሳ።”ትርጉም፦ቅዱስ፡ሩፋኤል፡ሆይ፡የጦቢትን፡ዐይኖች፡ለወሱ፡ጣቶችህ፡ሰላም፡እላለሁ።ለመፈወሱ፡በመተባበር፡የዓሣ፡ሐሞትን፡ለኳሉ፡ጥፍሮችህም፡ሰላም፡እላለሁ።ሩፋኤል፡ሆይ፡የኪሩቤል፡ወገን፡የምትሆን፡መለኮዊ፡ምሥጢርን፡የምትነግር፡ነህና።የሕይወት፡መልአክ፡እጅ፡የሱሳን፡ነቢይ፡እንደ፡ዳሰሰ።አቤቱ፡ጣቶችህ፡ዓይኖቼን፡ይዳስሱልኝ።መልክአ፡ቅዱስ፡ሩፋኤል። *”ሰላም፡ለሩፋኤል፡መልአከ፡ነፍስ”።ትርጉም፦የነፍስ(የሰውነት)መልአክ፡ለኾነ፡ለቅዱስ፡ሩፋኤል፡ሰላምታ፡ይገባል”። *”ሰላም፡ለመልከ፡ጼዴቅ፡ዐቢይ፡ካህን፡አምሳሊሁ፡ለወልደ፡እግዚአብሔር፤ዘእእመረ፡ምስጢሮ፡ኅቡአ፡ዘሀሎ፡ይትገበር”።ትርጉም፦ሊከናወን(ሊፈጸም)ዘንድ፡ያለውን፡ስዉር(ድብቅ)ምስጢሩን፡ያወቀ፤ለእግዚአብሔር፡ልጅ፡ምሳሌው፡ለኾነ፡ለታላቁ፡ካህን፡ለመልከ፡ጼድቅ፡ሰላም፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *የዕለቱ፡ዓራራይ፡ዜማ፦”ይቤሎ፡ለጦብያ፡አነ፡ውእቱ፡ሩፋኤል፡መልአክ፡አሐዱ፡እምሰብዓቱ(ተሰዓቱ)ሊቃ፡መላእክት፡ዘተፈኖኩ፡ኀበ፡ጦቢት”።ትርጉም፦ለጦብያ፡ከሰባቱ(ዘጠኙ)ሊቃነ፡መላእክት፡አንዱ፡ወደ፡ጠቢት፡የተላኩኝ፡ሩፋኤል፡መልአክ፡እኔ፡ነኝ፡አለው ። *የዕለቱ፡ምልጣን፡ግዕዝ፡ዜማ፦”ይሰግዱ፡በብረኪሆሙ፡ወያሌዕሉ፡ህሊናሆሙ፡በጥንቃቄ፡ወበኅሢሥ፡ኀበ፡እግዚኦሙ፡ንጉሥ፡ቀዋምያን፡ለነፍሳት፡እሙንቱ፡ሊቃናት፡ዑራኤል፡ወሩፋኤል፡ይትፌነው፡ለሣህል፡እምኀበ፡ልዑል”፡፡ትርጉም፦ወደ፡ጌታቸው፡ንጉሳቸው፡ይሰግዳሉ፡ህሊናቸውንም፡በጥንቃቄ ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋሉ፡ለነፍሳት፡የሚቆሙ፡እነዚህ፡አለቆች፡ዑራኤልና፡ሩፋኤል፡ከልዑል፡ለይቅርታ፡ይላካሉ፡፡ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”እግዚአብሔር፡ገሃደ፡ይመጽእ።ወአምላክነሂ፡ኢያረምም።እሳት፡ይነድድ፡ቅድሜሁ።“መዝ49፥2-3።የሚነበው፡ወንጌል፡ማቴ25፥31-46።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ያዕቆብ፡ዘሥሩግ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።