ዛሬ፡መስከረም13፡ቀን (23 Sept 2018)

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።
          *ዛሬ፡መስከረም13፡ቀን
*እንኳን፡ለታላቁና፡ቅዱስ፡የሆነ፡የቂሣርያ፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡ቅዱስ፡ባስልዮስ፡ላደረገው፡ተአምር፡ለመታሰቢያ፡በዓል(አንድ፡ጎልማሳ፡አገርልጋይ፡የጌታውን፡ልጅ፡ስወደዳት፡እርሷንም፡ከመውደዱ፡የተነሣ፡እርሷን፡ለማግባት፡ብሎ፡ወደ፡አንድ፡ከሀዲ፡ሥራየኛ፡ሔዶ፡እግዚአብሔር፡ክዶ፡በሰይጣን፡አምኖ፡በእጁ፡ፈርሞ፡ለሰይጣን፡ሰጠው፡ይህንን፡የጽሕፈት፡ደብዳቤ፡በእግዚአብሔር፡ኃይልና፡በጸሎቱ፡ቅዱስ፡ባስልዮስ፡በመደምሰስ፡ድንቅ፡ተአምር፡ያደረገበት፡ቀን)በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰበው፦ከከበረ፡ከባሕታዊ፡ከአባ፡ይስሐቅ፡ከመታሰቢያው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
 *”በዛቲ፡ዕለት፡እግዚአብሔር፡ገብረ።በእደ፡ባስልዮስ፡መንክረ።በአፍቅሮ፡ወለት፡አሐቲ፡ኀበ፡መሠርይ፡ዘሖረ።እንዘ፡ይከሥት፡በቅድመ፡ሕዝብ፡መጽሐፈ፡ክህደቱ፡ሥውረ።እምእደ፡ሰይጣን፡አንገፈ፡ወፄወወ፡ገብረ።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም13።
*መዝሙር ዘሰንበት(የዚህ፡ሳምንት፡መዝሙር)በ፭:እኩት፡አንተ፡ወስቡሕ፡ስምከ፡ወዓቢይ፡ኃይልከ፤ዘተዓርፍ፡በአርያም፡ወትሴባሕ፡በትሑታን፤ዘአንተ፡ሠራዕከ፡ሰንበተ፡ለዕረፍት፡ወወሀብከ፡ሲሳየ፡ዘበጽድቅ፡ለኲሉ፡እግዚኦ፡ባርክ፡ፍሬሃ፡ለምድር፤መሐሪ፡ወጻድቅ፡መኑ፡ከማከ፤ዘታርኁ፡ክረምተ፡በጸጋከ፡ነፍስ፡ድኅንት፡ወነፍስ፡ርኅብት፤እንተ፡ጸግበት፡ተአኲተከ።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ምድርኒ፡ወሀበት(ትሁብ)ፍሬሃ።ወይባርከነ፡እግዚአብሔር፡አምላክነ።ወይባርከነ፡እግዚአብሔር”።መዝ66፥6-7።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማር4፥24-39።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Comments are closed.