*እንኳን፡ለእግዚአብሔ፡ሰው፡ለሆነ፡ለየዋሁ፡ለቅኑ፡ለጻድቁ፡ለነቢያት፡አለቃ፡ለቅዱስ፡ሙሴ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለመጥምቀ፡መለኮት፡ለቅዱስ፡ዮሐንስ፡አባት፡ለበራክዩ፡ልጅ፡ለካህንና፡ለነቢዩ፡ለሆነ፡ለከበረ፡ለቅዱስ፡ዘካርያስ፡በንጉሥ፡ሄሮድስ፡እጅ፡ሰማዕትነት፡ለተቀበለበት፡ለዕረፍቱ፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከከበረ፡ዲማድዮስ፡ከግብጽ፡ደቡብ፡ደንጡ፡ከሚባ፡አውራጃ፡በሰማዕትነት፡ከዐረፈ፣ምግቡ፡የአጋዝን፡ወተት፡ከሆነ፡በዕረፍቱም፡ጊዜ፡ብዙ፡ተአምራትን፡ከአደረገ፡ከከበረ፡ከገዳማዊ፡ከቅዱስ፡ቂርቆስ፡ዕረፍት፣ከሰማዕቱ፡ሉክዮስ፡ከመታሰቢያው፣ከቅዱስ፡ኤርምያስና፡ከቅዱስ፡ዮሐንስ፣ከቅዱስ፡አንዲዎና፣ከቅዱስ፡ኤልያኖስና፡ከመነኰስ፡አሞንም፡ከመታሰቢያቸወ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለሙሴ፡ሊቀ፡ነቢያት፡ዘርእየ፡ሱራኄሁ፡ለጸባኦት፤ዘተመጠወ፡እምእደዊሁ፡ኦሪተ፡በጾም፡ወበጸሎት“።ትርጉም፦የሰራዊት፡ጌታን፡የብርሃን፡ወገግታ፡ያየ፤በጾምና፡በጸሎት፡ከእጆቹም፡ኦሪትን(ሕግን)ለተቀበለ፡ለሊቀ፡ነቢያት፡ለሙሴ፡ሰላምታ፡ይገባል። *”ሰላም፡ለዘካርያስ፡ካህን፡ወነቢይ፡ዘርእዮ፡ለካህን፡ዐቢይ፡ዘስሙ፡ዮሴዕ፡ዘይነብር፡ውስተ፡ምሥዋዒሁ፡ለእግዚብሔር”።ትርጉም፦በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ውስጥ፡ስሙ፡ዮሴዕ፡የሚባል፡ታላቁን፡ካህን፡ተቀምጦ፡ላየው፡ለካህኑና፡ለነቢዩ፡ዘካርያስ፡ሰላምታ፡ይገባል። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ካህናቲከ፡ይለብሱ፡ጽድቀ።ወጻድቃኒከ፡ትፍሥሕተ፡ይትፌሥሑ።በእንተ፡ዳዊት፡ገብርከ”።መዝ131፥9-10፡ወይም፡መዝ57፥10-11።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ23፥29-39።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ኤጲፋንዮስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁ­ላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*እንኳን፡ስለ፡ተዋሕዶ፡ሃይማኖት፡በአርዮሳዊያን፡ጢሙን፡ለተነጨና፡ጥርሱንም፡ለተነቀለ፡ለታላቁ፡ሊቅ፡ለእስክድርያ፡ሃያ፡አምስተኛ፡ኤጴስቆጶስ፡ለአቡነ፡ዲዮስቆሮስ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለእመቤታችን፡እናት፡ለቅድስት፡ሐና፡የልደቷ፡በዓል፡መታሰቢያ፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከመጥምቀ፡መለኮት፡እናት፡ከቅድስት፡ኤልሳቤጥ፡ከመታሰቢያዋ፣ከገቡላ፡ኤጴስቆጶስ፡ከከበረ፡አባት፡ከአባ፡ሳዊርያኖስ፡ዕረፍት፣ከከበሩ፡አጋቶንና፡ጴጥሮስ፡ከዮሐንስና፡ከአሞን፡ከእናታቸው፡ራፈቃ፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፣ከቅዱስ፡ፋሲለደስ፡ጋር፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፡ከሁለት፡ሺህ፡ሰዎች፣ከጋንግራ፡ሰው፡ዳሳ፣ከአንጾኪያ፡ኤጲስቆጶስ፡ከናውላ፣ከመነኵሴውም፡ከጴጥሮስ፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለዲዮስቆሮስ፡ዘተመልኀ፡ጥረሲሁ፤ወተነጽየ፡ጽሕሙ፡ለክርስቶስ፡በእንተ፡ስሙ”።ትርጉም፦በክርስቶ፡ስም(ስለክርስቶስ፡ስም)ጢሙን፡የተነጨ፤ጥርሱንም፡የተነቀለ፡ለኾነ፡ለዲዮስቆሮስ፡ሰላምታ፡ይገባል። *”ሰላም፡ለሐና፡እንተ፡ወለደታ፡ለማርያም፡ዘኮነት፡ተንከተመ፡ጽድቅ፡በኵሉ፡ዓለም፤ድንግል፡ወእም፤ወላዲቱ፡ለፀሓይ፡ዳግሚት፡ሰማይ”።ትርጉም፦ፀሓይን፡የወለደችው፡ኹለተኛዪቱ፡ሰማይ፤ድንግልም፡እናትም፤ለዓለሙ፡ኹሉ፡የእውነት፡ድልድይ(መሸጋገሪያ)የኾነችዪቱን፡ማርያምን፡ለወለደቻት፡ለሐና፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *”ሰላም፡ለዲዮስቆሮስ፡ሃይማኖተ፡ንጉሥ፡ዘተሣለቀ።ተዋሕዶተ፡አምላክ፡ወሰብእ፡አመ፡ለክልኤ፡ነፈቀ።ያስተጻንዕ፡ህየ፡እለ፡ሀለዉ፡ደቂቀ።ዘተነጽየ፡እምነ፡ጽሕሙ፡ወእምአስናኒሁ፡ዘወድቀ።ፍሬ፡ሃይማኖቱ፡ፈነወ፡ብሔረ፡ርኁቀ”።ትርጉም፦ሰው፡የኾነ፡የአምላክን፡ተዋሕዶ፡ለኹለት፡በከፈለ፡ጊዜ፡በንጉሥ፡ሃይማኖት፡ላይ፡የተሣለቀ፡ለኾነ፡ለዲዮስቆሮስ፡ሰላምታ፡ይገባል፤በዚያ፡ያሉትን፡ልጆች፡ያጽናና፡ዘንድ፡ከወደቁ፡ጥርሶቹ፡ከተነጨ፡ጽሕሙ፡የሃይማኖት፡ፍሬ፡አድርጎ፡ወደ፡ሩቅ፡ሀገሩ፡ላከ።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም7። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”እስመ፡መምህረ፡ሕግ፡ይሁብ፡በረከተ።ወየሐውር፡እምኀይል፡ውስተ፡ኃይል።ወያስተርኢ፡አምላከ፡አማልክት፡በጽዮን”።መዝ83፥6-7።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማር1፥23-29።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የእመቤታች፡ማርያም፡ቅዳሴ­፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁ­ላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*እንኳን፡ከዐበይት፡ነቢያት፡አንዱ፡ለሆነው፡ለታላቁ፡ነቢይ፡ለአሞጽ፡ልጅ፡ለቅዱስ፡ኢሳይያስ፡የዕረፍት፡በዓል።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳር፡ከሚታሰቡ፦ከቅድስት፡ሰብልትንያ፡በከሀዲ፡ንጉሥ፡በዲዮቅልጥያኖስ፡ዘመን፡በሰማዕትነት፡ከዐረፋች፣ከመነኰስ፡ያዕቆብ፣ከኤጲስቆጶስ፡ከአናቲሞስ፣ከባስሊስና፡ከአሮጦስ፣ከውርዋና፣ከሳውልስ፣ከሰማዕቱ፡ከሰውላስም፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለኢሳይያስ፡ነቢይ፡ወልደ፡አሞጽ፡ዘፈጸመ፡ገድሎ፡በሞሠርተ፡ዕፅ፡ደራሲ፡ትንቢተ፡እምነቢያት፡ልዑላተ”።ትርጉም፦በዕንጨት፡መጋዝ፡ተተርትሮ፡ገድሉን፡የፈጸመ፡ለኾነ፤ከታላላቆች(ከዐበይት)ነቢያት፡ይልቅ፡ትንቢትን፡ለጻፈ፡ለነቢዩ፡ለኢሳይያስ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *መዝሙር፡ዘሰንበት(የዚህ፡ሳምንት፡መዝሙር)፦በ፭: ዮሐንስ፡አኅድዓ፡እምካልአኒሁ፡አንሐ፡ወክሐ።እንዘ፡ይብል፡እምላዕሉ፡ወረደ፡ቃለ፡አብ።ወተሐውከ፡ማየ፡ዮርዳኖስ፡እምግር፡መለኮት።ወደንገጹ፡ኲሉ፡ኃይለ፡ሰማያት፡ወምድር።ከማሁ፡ኮነ፡በቢታንያ፡በቤተ፡ራባ፡በማዕዶተ፡ዮርዳኖስ።ወሶበ፡ርእዮ፡ዮሐንስ፡ለኢየሱስ፡ከልሐ፡ወይቤ፡ነዋ፡በግዑ፡ለእግዚአብሔር።ይቤሎ፡ኢየሱስ፡ለዮሐንስ፡አጥምቀኒ፡በማይ፡ከመ፡ይትቀደስ፡ማይ፡በማዕተበ፡ሰማይ።አጥመቆ፡ዮሐንስ፡ለኢየሱስ።በፈለገ፡ዮርዳኖስ።እምድኅረ፡አጥመቀ፡ለሊሁ፡ተጠምቀ።ምህሮሙ፡ለሕዝቡ፡ወይቤሎሙ፡አክብሩ፡ሰንበተ፡ተገበሩ፡ጽድቀ።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ሣህል፡ወርትዕ፡ተራከባ።ጽድቅ፡ወሰላም፡ተሰዐማ።ርትዕሰ፡እምድር፡ሠረፀት”።መዝ84፥10-11፡ወይም፡መዝ104፥14-15።የሚነበበው፡ወንጌል፡ዮሐ1፥15-38፡ወይም፡ዮሐ12፥36-50።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡አትናቴዎስ፡ወይም፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን። ✞አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ✞ ዛሬ መስከረም 6 የዋልድባው የአቡነ ሳሙኤል ዐፅማቸው የፈለሰበት ነው፡፡ ጻድቁ ገና በ12 ዓመታቸው ማይ ሹም በተባለው ባሕር ገብተው ሲጸልዩ ባሕሩ በብርሃን ተከቦ ይታይ ነበር፡፡ ከባሕሩም ወጥተው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው እያለቀሱና እያዘኑ ሲጸልዩ ካህናቱ ‹‹ይህ ሕፃን የእኛ ኃጢአት እየታየው? ወይስ ምን ኃጢአት ኖሮበት ነው እንዲህ የሚያዝነውና የሚያለቅሰው?›› እያሉ […]

Continue reading

*እንኳን፡ታላቁን፡አስገራሚውን፡ጣራዊ፡ክፍት፡ሆኖ፡ዝናብ፡የማይገባው፡ቤተ፡መቅደስ፡ለአነጹ፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡አሮን፡ዘመቄት(መንክራዊ)፡የዕረፍት፡በዓል፣እግዚአብሔር፡ለሚወድ፡ሃይማኖቱ፡ለቀና፡ለኢትዮጵያዊው፡ንጉሥ፡ለአፄ፡ልብነ፡ድንግል፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለአቡነ፡ገብረ፡ኢየሱስ፡ዘጎንደር፡የልደት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከከበረች፡ሶፍያ፡ከሁለት፡ልጆቿ፣ከአክሶስናና፡ከበርናባ፡ከሚባሉት፡በሰማዕትነት፡ከዐረፋ፡ና፡ከሰማዕቱ፡ቅዱስ፡ማማስ፡ዕረፍት፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *አቡነ፡ገብረ፡ኢየሱስ፡ዘጎንደር፦የትውልድ፡ሀገራቸው፡ጎንደር፡ፎገራ፡ሲሆን፡መስከረም5፡ቀን፡ተወለዱ።ጻድቁ፡የሚታወቁት፡አንድ፡ትልቅ፡ግብር፡አላቸው።እርሱም፡ጥርሳቸው፡እያበራ፡ለቤተ፡ክርስቲያን፡አገልግሎት፡ይሰጥ፡ነበር።መነኮሳቱ፡በጥርሳቸው፡ብርሃ፡ብቻ፡አገልግሎት፡ያካሄዱ፡ነበር።ጻድቁ፡ሲያርፉም፡ጥርሳቸው፡የ6፡ሰዓት፡መንገድ፡ተሂዶ፡ሲያበራ፡ታይቷል።በጻድቁ፡ስም፡የተጠሩ፡ገዳማት፡በትግራይና፡ሽሬና፡በጎንደር፡ይገኛል።ዕረፍታቸው፡መጋቢት5፡ነው።ምንጭ፡መዝገበ፡ቅዱሳንና፡ቅዱሳን፡በዓላት። “ሰላም፡ለማማስ፡ሰማዕተ፡ወልድ፡ዘአቑረራ፡ለነድ፡ዘሎቱ፡አንበሳ፡ይሰግድ”።ትርጉም፦አንበሳ፡ለሚሰግድለትና፡ነበልባልን፡ላቀዘቀዛት፡የወልድ፡ምስክር፡ለኾነ፡ለማማስ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *”ሰላም፡እብል፡ለማማስ፡ምቱር።በስይፍተ፡መንገን፡በሊሐት፡ወበመንኰራኵር፡፡ዝንቱ፡መዋዒ፡ሶበ፡ጸለየ፡በደብር።ተውህበ፡ሎቱ፡እምሰማይ፡በትር።ወበዘቢቢጦቱ፡ማየ፡አውጽአ፡እምድር”።ትርጉም፦ስሎች፡በኾነ፡የመዘውር፡ሰይፎች፡እና፡በመንኰራኵር፡የተቆረጠ፡ለኾነ፡ለማማስ፡ሰላም፡እላለኊ፤ይኽ፡አሸናፊ፡በተራራ፡ላይ፡በጸለየ፡ጊዜ፡ከሰማይ፡ለርሱ፡በትር፡ተሰጠለት፤በምቱም፡ውሃን፡ከምድር፡አወጣ።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም5። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”አዋልደ፡ንግሥት፡ለክብርከ።ወትቀውም፡ንግሥት፡በየማንከ።በአልባሰ፡ወርቅ፡ዑጽፍት፡ወኊብርት”።መዝ44፥9።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ13፥31-44።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የሠለስቱ፡ምዕት፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*እንኳን፡ከግብጽ፡ለኢትዮጵያ፡ሊቀ፡ጳጳስ፡ተሾመው፡ለመጡ፡በኢትዮጵያ፡ብዙ፡የዋሻ፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ላነጹ፡ለብጹዓዊ፡አቡነ፡ሙሴ፡ዘድባ፡የዕረፍት፡በዓል፣ለወንጌላዊው፡ቅዱስ፡ዮሐንስ፡የልደት፡በዓልና፡ለነዌ፡ልጅ፡ለቅዱስ፡ኢያሱ፡ለመታሰቢያ፡በዓሉ፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከእስክንድርያ፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡ከአባ፡መቃርስ፡ዕረፍትና፡በአንጾኪያ፡በሰማዕትነት፡ከሞቱ፡ከ2መቶ፡ሰዎች፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *ብጹዕ፡አቡነ፡ሙሴ፡ዘድባ፦በአባታቸው፡የእቤታችን፡ጠባቂ፡የአረጋዊ፡ቅዱስ፡ዮሴፍ፡የልጅ፡ልጅ፡ሲሆኑ፤በእናቸው፡በኩል፡ድንግል፡ማርያም፡ከልጇ፡ጋር፡በቃና፡ዘገሊላ፡ሰርግ፡የተገኘችበት፡የዶኪማስ፡የልጅ፡ልጅ፡ናቸው።የአባታቸው፡ስም፡ቅዱስ፡ዮስጦስ፡ሲባል፤የእናታቸው፡ስም፡ቅድስት፡ጵስርስቅላ(ሶልያና፡ማርያም)ይባላል። በሊቀ፡መላእክት፡ቅዱስ፡ገብርኤል፡አብሳሪነት፡ታህሣሥ8፡ተወለዱ።በዚህች፡ቀን፡ከእናታቸው፡እቅፍ፡በመውረድ፡ለአብ፡ለወልድ፡ለመንፈስ፡ቅዱስ፡ምስጋና፡ይሁን፤ከጨለማ፡ወደ፡ብርርሃን፡ላወጣኸኝ፡ብለው፡ፈጣርያቸውን፡አመስግነዋል።በ40ኛው፡ቀን፡የጌታ፡ሐዋርያት፡ጴጥሮስ፣ያዕቆብ፣ፊሊጶስና፡እንድርያስ፡ሆነው፡ጥር18፡ክርስትናን፡አቡነ፡ሙሴን፡አነሱዎቸው።በ3፡ዓመታቸው፡ወላጆቻቸው፡ለቤተ፡ከክርስቲያን፡ሰጧቸው።ቅዱስ፡ፋኑኤልና፡ቅዱስ፡ዮናኤል፡ሕብስት፡ሰማያዊ፡እያመጡ፡ይመግቧቸው፡ነበር።ከዚህ፡በኋላ፡መምህራቸው፡ዝክረ፡ጻድቅ፡ብሉያትንና፡ሐዲሳትን፡አስተማራቸው።በወንጌላዊው፡በቅዱስ፡ማርቆስ፡እጅ፡ዲቁና፡ተሾሙ።እመቤታችን፡ማርያምም፡ለብፁዓዊ፡ሙሴ፡ልፋፈ፡ጽድቅ፣ሰኔ፡ጎልጎታን፣ባርቶስና፡ራዕየ፡ማርያምን፡ሰታቸዋለች።ወገባቸውን፡ከጠጉር፡በተሰራ፡መታጠቂያ፡ይታጠቁ፡ነበር።አቡነ፡ዘበሰማያትም፡በጀመሩ፡ጊዜ፡ሰባቱ፡ሰማያት፡ተከፍተውላቸው፡ከአጋዕዝተ፡ዓለም፡ሥላሴ፡ጀምሮ፡ሁሉንም፡ቅዱሳን፡በግልጥ፡ያያሉ።ሲሰግዱ፡እንባቸው፡ደረታቸውና፡እግራቸውን፡እያራሰ፡በመሬት፡ይፈሳል።በዓለም፡ብዙ፡የዋሻ፡ቤተ፡ክርስቲን፡አንጸዋል።የሕንፃ፡ሥራ፡ከመደመራቸው፡በፊት፡40ቀን፡ይጾማሉ።ሁለቱ፡መላእክት፡ቅዱስ፡ፍርክኤልና፡ቅዱስ፡ፍናኤል፡እየረዷቸው፡መቅደስን፡ያንጻሉ።የዋሻ፡ቤተ፡መቅደስ፡ስራ፡ጎን፡ለጎን፡መስቀልና፡ሌሎች፡ንዋየ፡ቅዱሳት፡ይሰራሉ።የሚሰሯቸው፡መቅደሶች፡ከፊሉ፡የሚታዩ፡ምዕመናን፡የሚገለገሉባቸው፡ሲሆን፡የቀሩት፡የማይታዩ፡ስውራን፡የሚገለገሉበት፡ነው። አቡነ፡ሙሴ፡ጵጵስና፡የተሾሙት፡በ12ቱ፡ሐዋርያት፡በአንድነት፡ነው።ዘመናቸውን፡ሁሉ፡ከ24ቱ፡ካህናተ፡ሰማይ፡ጋር፡በመሆን፡የአብ፡የወልድ፡የመንፈስ፡ቅዱስን፡መንበር፡አጥነዋል።በድንግልናቸው፡በንጽሕናቸው፡የከበሩ፡12ክንፍ፡የተጎናጸፉ፡ናቸው።ጥቂቶች፡ለማየት፡የታደሉትን፡ብሔረ፡ብፁዓን፡ሄደው፡አይተዋል። አቡነ፡ሙሴ፡በግብፅና፡በእስራኤል፡መካከል፡ሲካር፡በሚባል፡ቦታ፡ካገለገሉ፡በኋላ፡ጣዖታትን፡ለማሳፈር፡ወደ፡መቄዶንያ፡ሄደው፡ጣዖት፡አምላኪውን፡ንጉሥ፡ገሰጹት።ንጉሥ፡ተቆጥቶ፡አጥንታቸው፡እስኪሰበር፡ድረስ፡በብረት፡አስደብድቦ፡በብረት፡አልጋ፡ላይ፡አስተኝቶ፡እሳት፡አነደደባቸው።ቅዱስ፡ሚካኤልና፡ገብርኤል፡ግን፡ዳሰው፡ፈወሷቸው።በማግስቱ፡ወደ፡ፍርድ፡አደባባይ፡ቢወስዷቸው፡ምንም፡እንዳልሆኑ፡ንጉሡ፡በማየቱ፡በንዴት፡ሰውነታቸውን፡በሰይፍ፡አስቆራረጠ።ከሰውነታቸው፡ደም፣ውሃ፣ወተትና፡መዓር፡ወጣ።ጌታችንም፡አድኗቸው፡በስምህ፡የተማፀነውን፡መልካም፡ነገር፡አደርግታለሁ፡ብሎ፡ቃል፡ኪዳን፡ገባላቸው።በግብፅ፡አንስጣስዮስ፡ቴዎዶስዮስ፡ተብለው፡ሲነግሱ፡መላእክት፡የአባቱ፡የዳዊት፡መንግሥት፡ቅባት፡ቀቧቸው፤የመንግሥት፡ልብስ፡አለበሷቸው፤የመንግሥት፡ሥርዓትን፡ሁሉ፡ሰጧቸው።የጣዖታትን፡ቤት፡አፍርሱ፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ሥሩ፡በማለት፡ሕዳር12፡አዋጅ፡ነጋሪን፡ላኩ።ጌታችን፡በግብፅ፡ተሶዶ፡ሳለ፡ለአረጋዊ፡ቅዱስ፡ዮሴፍ፡የተናገረው፡ትንቢት፡ተፈፀመ”ከልጅህ፡የሚወለድ፡በግብፅ፡ያሉትን፡ጣዖቶች፡አፍርሶ፡ሐይማኖትን፡ያጸናል”፡ብሎ፡ነበር።እዲሁም፡ቅድስት፡አርሴማ፡ሳትወለድ፡በስሟ፡የተሰየመውን፡ታቦት፡በግብፅ፡ያገኙና፡ያከበሩ፡ናቸው(ገድለ፡አርሴማ፡7ኛ፡ተዓምር)። በግብፅ፡ደብረ፡ምጥማቅ፡ማርያም፡በመጀመሪያ፡ሰርተው፡የቀደሱት፡አቡነ፡ሙሴ፡ናቸው።በተጨማሪ፡ብዙ፡የህንጻ፡ቤተ፡ክረስቲያንና፡የዋሻ፡ቤተ፡ክረስቲያን፡አንጸዋል።እንደ፡ቅዱሳን፡ብዙ፡ድንቅ፡ተዓምር፡አድርገዋል።ለምሳሌ፡አውሬ፡ገድሏቸው፡ተጠራቅሞ፡የነበረ፡አፅም፡ላይ፡ጸልየው፡አራት፡ሺህ፡የሞቱ፡ሰዎችን፡ከሞት፡አስነስዋል።40ዓመት፡በንግሥና፡ከቆዩ፡በኋላ፡ከብዙ፡ተከታዮቻቸው፡ጋር፡ወደ፡አስቄጥስ፡ገዳም፡ለምነና፡ስጓዙ፡በበረሃው፡ተርበው፡ለወደቁት ወደ፡እግዚአብሔር፡ሲጸልዩ፡መና፡ወርዶላቸው፡መግበዋል፡አስቄጥስ፡ገዳም፡ሲደርሶ፡አቡነ፡መቃርስ፡ነበሩ፡የተቀበሏቸው፡፡አቡነ፡ሙሴ፡በአስቄጥስ፡በአቡነ፡እንጦንስ፡ስም፡የመጀመርያውን፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ሰርተው፡ከፈፀሙ፡በኋላ፡አቡነ፡እንጦንስንና፡አቡነ፡መቃርስ፡በምንኵስና፡ልብስ፣በመላእክት፡አስኬማ፣በቅንዓት፣በቀሚስና፡በቆብዕ፡ላይ፡ለ40ቀን፡ጸልየው፡ጥር22፡ተክለማርያም፡ብለው፡ሰይመው፡አመነኮሷቸው።በዚያውም፡አቡነ፡መቃርስ፡ከበታቻቸው፡ብፁዓዊ፡ሙሴን፡ሾሙ።በአስቄጥስ፡ብዙ፡ተከታዮቻቸውን፡አመንኵሰው፡ቀድሞ፡ወደ፡ሰሯቸው፡ቤተ፡መቅደሶች፡ይልኳቸው፡ነበር።የቀሩት፡ደግሞ፡በኋላ፡ወደ፡ኢትዮጵያ፡ሲመጡ፡አብረዋቸው፡መጥተዋል። የኢትዮጵያ፡የመጀመርያው፡ጳጳስ፡አቡነ፡ሰላማ፡በማረፋቸው፡ሁለቱ፡ቅዱሳን፡ነገሥታት፡አብርሃ፡ወአጽብሃ፡ጳጳስ፡እንዲልኩላቸው፡ከእጅ፡መንሻ፡ጋር፡ወደ፡ግብፅ፡ላኩ።አቡነ፡አትናቴዎስ፡ፈቃደ፡እግዚአብሔር፡ጠይቀው፡አቡነ፡ሙሴ፡ከአስቄጥስ፡ገዳም፡ለኢትዮጵያውያን፡አባት፡እዲሆኑ፡አቡነ፡ሚናስ፡ብለው፡ሾሙ።ከሶስት፡ሺህ፡ልጆቻቸው፡ጋር፡ሆነው፡ብዙ፡ቅርስ፡ይዘው፡አባታችን፡ወደ፡ኢትዮጵያ፡ሲመጡ፡ህዝቡ፡በደስታ፡ተቀበሏቸው።ብዙ፡መጽሐፍትን፡ከአረብኛ፡ወደ፡ግእዝ፡ቋንቋ፡ተርጉመው፡ጽፈዋል።ይጽፉበት፡የነበረው፡ብዕር፡አድሮ፡በማግስቱ፡ለምልሞ፡አብቦ፡ይገኛል።ቀለም፡ይበጠብጡበት፡የነበረው፡የቀንድ፡ዋንጫም፡ከመሬት፡ተጣብቆ፡ያገኙት፡ነበር።በእጃቸው፡ሲያላቅቁት፡ከመሬት፡ጠበል፡ይፈልቃል፣በጠበሉም፡ህሙማንን፡ፈውሰውበታል። በኢትዮጵያ፡አምስት፡መቶ፡የዋሻ፡ቤተ፡ክስቲያን፡ያነጹ፡ሲሆን፡በአጠቃላይ፡በመላው፡ዓለም፡ከዐሥር፡ሺህ፡በላይ፡ቤተ፡ክርስቲያ፡ሰርተዋል፣አንጸዋል(መለከት፡መጽሔት፡2007ዓ.ም)።በእንቁና፡በእብነ፡በረድ፡ከሰራቸው፡ቤተ፡ክረስቲያኖች፡መካከል፡በአራራት፡ደብር(ከምድር፡ጥፋት፡በኋላ፡የኖኅ፡መርከብ፡መጀመርያ፡ያረፈችበት)በጻድቁ፡ኖኅ፡ስም፣አብርሃም፡ሥላሴን፡በድንኳኑ፡ባስተናገደበት፡ስፍራ፡በቅድስት፡ሥላሴ፡ስም፣በሕንድ(በሐዋርያው፡ቅዱስ፡ቶማስ፡መቃብር፡ቦታ)በቅዱስ፡ቶማስ፡ስም፣በአርማንያና፡በግርስ(በሰማዕቱ፡ቅዱስ፡ጊዮርጊስ፡ስጋውን፡ባሳረፉበት፡ቦታ)በቅዱስ፡ጊዮርጊስ፡ስም። *በኢትዮጵያ፡በአቡነ፡ሙሴ፡ከታነጹት፡ቤተ፡ከርስቲያ፡ውስጥ፡የተወሰኑት፦ 1.የድባ፡መቅደሰ፡ማርያም፡አቡነ፡ሙሴ፡አንድነት፡ገዳም(ባለ፡ሰባት፡መቅደስ፡ፎቅ)፣የረፍታቸው፡ቦታ፣በትረ፡ሙሴያቸውና፡የእጅ፡መስቀላቸው፡ያለበት(ሰሜን፡ወሎ፡ዳውንት) 2.ደብረ፡ከርቤ፡ግሸን፡ማርያም፡ላይ፡በምስራቅ፡በኩል፡ስውር፡ቤተ፡መቅደስ(ድርሳነ፡ራጉኤል) 3.አእማድ፡ቅድስት፡ሥላሴ፡ገዳም(መቄት)እንደ፡አቡነ፡አሮን፡መንክራዊ፡ጣራው፡ክፍት፡ሆኖ፡ዝናብ፡የማይገባው፣ በመጨረሻ፡ብጹዕ፡አቡነ፡ሙሴ፡በቤተ፡ሚናስ፡ቤተመቅደስ፡የድባ፡መቅደሰ፡ማርያም፡አቡነ፡ሙሴ፡ገዳም፡መሰከረም4፡በዕለተ፡እሁድ፡አረፋ።ወርሃዊ፡በዓላቸው፡ወር፡በገባ፡በ4፡ነው።በተለይ፡ጋብቻን፡የሚቀድሱ፣ክህነት፡የሚባርኩ፣መናንያንን፡የሚያጸኑ፡አረጋዊን፡አባት፡ናቸው።ምንጭ፡የድባ፡መቅደሰ፡ማርያም፡አቡነ፡ሙሴ፡አንድነት፡ያሳተመው፡መጽሔት። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወወሀብኮሙ፡ትእምርተ፡ለእለ፡ይፈርሁከ።ከመ፡ያምሥጡ፡እምገጸ፡ቅስት።ወይድኀኑ፡ፍቁራኒከ”።መዝ59፥9-10።የሚነበበው፡ወንጌል፡ዮሐ6፥1-22።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የሠለስቱ፡ምዕት፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*እንኳን፡ለኢትዮጵያዊው፡ጻድቅ፡የስውራን፡ቅዱሳን፡አባቶች፡መኖርያ፡የሆነውን፡በሱማሌ፡ክልል፡በርሃ፡ውስጥ፡የሚገኘው፡ታላቁ፡ገዳም፡ደብረ፡ሐዘሎን፡ለመሰረቱት፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡አንበስ፡ዘአዘሎ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለገዳመ፡ሲሐት፡ለአባ፡ሙሴ፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦የከበረ፡አባት፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡አባ፡ዲዮናስዮስ፡ከተሾመ፡በሁለተኛው፡ዓመት፡፡በእስክድርያ፡ከተማ፡የኤጲስቆጶሳት፡የአንድነት፡ጉባኤ፡ከተደረገበት(ይህም፡ጉባኤ፡የሆነው፡ነፍስ፡ከሥጋዋ፡ጋር፡ትሞታለች፡በዕለተ፡ትንሣኤም፡ከሥጋዋ፡ጋር፡አብራ፡ትነሣለች፡ስለሚሉ፡ክፋዎች፡በዐረቢያ፡አገር፡ስለ፡ተነሡ፡ሰዎች፡ነው)፣ከሰማዕት፡አባ፡ዲዮስቆሮስ፣ሰማዕት፡ከሆነ፡ከሊቀ፡ጳጳሳት፡ዲዮናስዮስ፣ከዲያቆን፡በትንከልና፡ከብዙዎች፡ከፋርስ፡ሰማዕታት፡ከዕረፍታቸው፡መታሰቢያ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለአባ፡አንበስ፡ዘከለሎ፡ሞገስ”።ትርጉም፦በሞገስ፡የጋረደው፡ለኾነ፡ለአባ፡አንበስ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *”ሰላም፡ለአባ፡አንበስ፡በፍኖተ፡ፃማ፡ወሥራሕ።ዘይጼዓን፡ዘልፈ፡ዲበ፡አንበሳ፡መፍርህ።ለዘይጸድቅ፡ብእሲ፡ይገብእ፡ፍትሕ።ኢያጠፍኦ፡ማይ፡ወርደተ፡ዝናም፡ብዙኅ።ለዓሠረ፡ደሙ፡ቀይሕ፡ዘሀሎ፡በኰኵሕ”።ትርጉም፦በሚያደክምና፡በሚያዝል፡ጎዳና፡ላይ፡አስፈሪ፡በኾነ፡አንበሳ፡ዘወትር፡የሚጫን፡ለኾነ፡ለአባ፡አንበስ፡ሰላምታ፡ይገባል፤እውነተኛ፡ለኾነ፡ሰው፡ፍርድ፡እስኪደረግ፡ድረስ፡በዐለት፡ላይ፡ቀይ፡የደሙን፡ምልክት፡የውሃና፡የበዛ፡ዝናም፡አወራረድ፡አያጠፋውም። *”ሰላም፡ለሙሴ፡ዘረሰየ፡እምዓለም፡ተፈልጦ።ቔጽለ፡ሆሣዕና፡አራዘ፡ወፍሬ፡ዘይቶን፡ሥብጦ።በብዙኅ፡መከራ፡እምድኅረ፡ሰይጣን፡አስፈጦ፧እግዚአብሔር፡መሐሪ፡መንገለ፡ገዳም፡ሜጦ።ኀበ፡ሥጋሁ፡የዓርፍ፡ወነፍሶ፡ይትሜጦ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም3። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”እስመ፡አድኀንካ፡ለነፍስየ፡እሞት።ወለአዕይትየኒ፡እምአንብዕ።ወለእገርየኒ፡እምዳኅፅ”።መዝ55፥13-14።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ18፥18-23።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዲዮስቆሮስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Continue reading

*እንኳን፡ለታላቁ፡ነብይ፣ሰማዕት፣ሐ­ዋርያ፣ካህን፡ለመጥምቀ፡መለኮት፡ቅ­ዱስ፡ዮሐንስ፡ሕግ፡አፍራሽ፡በሆነ፡­በንጉስ፡ሄሮድስ፡እጅ፡አንገቱን፡በ­መሰየፍ፡ሰማዕትነት፡ለተቀበለበት፡­በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በዚች፡ቀ­ን፡በጨማሪ፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦በግብጽ፡ውስጥ፡ታዕዳ፡ከሚባል፡አገር፡በሰማዕትነት፡ከዐረፈ፡ከቅዱስ፡ዳስያ፣ከሰ­ማዕት፡ዲዲሞስና፡ቅድስት፡መሪና፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በ­ረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለዮሐንስ፡ግፋዕ፡ወቅቱል፡ንጹሕ፡ወቅዱስ፡ወስቡሕ፡ላእክ፡ወነቢይ፡ወሰማዕት፡ድንግል፡ካህን፡ጸያሒ፡ወሰባኪ፡መጥምቀ፡እግዚኡ”።ትርጉም፦ጌታውን፡ያጠመቀና፡ሰባኪ፤መንገድ፡ጠራጊ፣ካህን፡ድንግል፡ሰማዕት፣ነቢይና፡አገልጋይ፤ምስጉን፡ቅዱስና፡ንጹሕ፤ተገፍቶ፡የተገደለ፡ለኾነ፡ለቅዱስ፡ዮሐንስ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *የዕለቱ፡ምልጣን፡ግእዝ፡ዜማ፦ሃሌ፡ሉያ­”እምኄሶ፡ለሄሮድስ፡ይብላዕ፡መሐላ­ሁ፡እምያምትር፡ርዕሶ፡ለዮሐንስ፡ዐ­ቢይ፡ነቢይ፡ሰባኬ፡ጥምቀት፡ለንስሐ፡ከመ፡ይመኑ፡ህዝብ፡በብርሃኑ።”ትርጉ­ም፦ሄሮድስ፡ከፍ፡ያለ፡ነቢይ፡ህዝቡ፡በብርሃኑ(በጌታች፡በአምላካች፡በመድኃኒታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ)፡ያምኑ፡ዘንድ፡ለንስሐ፡የሚሆን፡ጥምቀ­ትን፡የሚሰብክ፡የዮሐንስን፡ራስ፡ከ­ሚቆርጥ፡መሐላውን፡ቢበላ፡በተሻለው­፡ነበር።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወይርአ­ዩ፡አሕዛብ፡በቅድመ፡አዕይንቲነ።በ­ቀለ፡ደሞሙ፡ለአግብርቲከ፡ዘተክዕወ­።ይባዕ፡ቅድሜከ፡ገዐሮሙ፡ለሙቁሓን”።መዝ78፥10-11።የሚነበበው፡­ወንጌል፡ማርቆስ6፥14-30።የሚቀ­ደሰው፡ቅዳሴ፡የዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎ­ድጓድ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡­ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

*እንኳን፡ለርእሰ፡ዓውደ፡ዓመት፡ለቅዱ­ስ፡ዮሐንስ፡አደረሰን።(ከዘመነ፡ቅዱስ፡ማርቆስ፡ወደ፡ዘመነ፡ቅዱስ፡ሉቃስ፡በሰላም፡አሸጋገረን)፣ለመላእክት፡አለቃ፡ለቅዱስ፡ራጉ­ኤል፡ለበዓለ፡ሲመቱ፣ለሐዋርያው፡ለቅ­ዱስ፡ለርተሎሜዎስ፡በዓለ፡ዕረፍቱ፣ለታ­ላቁ፡አባት፡ለቁልዝም፡ሰው፡ለሆነ፡­ፍፁም፡ፃድቅ፡ለአባ፡ሚልኪ፡በዓለ፡ዕ­ረፍት፡­፡በተጨማሪ፡በዚች፡በሰንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከሦስተኛ፡የእስክድርያ፡ሊቀ­፡ጳጳስ፡ከአባ፡ሚልዮስ፡በዓለ፡ዕረ­ፍትና፡ከቅዱስ፡ኢዮብ፡በፈሳሽ፡ውኃ፡ታጥቦ­፡ከደዌው፡ሁሉ፡ከዳነበት፡ቀን፣ረድኤት፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ለራጉኤል፡ወለሳቁኤል፤ለአፍኒን፡ወለራሙኤል፡እለ፡የዐውዱ፡መንበሮ፡ለልዑል”።ትርጉም፦የልዑል፡ዙፋኑን፡ለሚዞሩ፡ለራጉኤልና፡ለሳቁኤል፤ለአፍኒንና፡ለራሙኤል፡ሰላምታ፡ይገባል፡፡አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ። *”ባርክ፡ለነ፡እግዚኦ፡ዘንተ፡ዓመተ­፡ምሕረትነ፡በብዝሃ፡ኂሩትከ፡ለሕዝ­ብከ፡ኢትዮጵያ፡ከመ፡ንግነይ፡ለስም­ከ፡ቅዱስ፡ወከመ፡ይኩን፡ንብረተነ፡­በሰላም፡ወባዳኅና፡በዝንቱ፡ዓመት።­”ትርጉም፦ባርክልን፡አቤቱ፡ይህንን­፡የምሕረት፡ዓመታችን፡በቸርነትህ፡­ብዛት፡ለሕዝቦችህ፡ኢትዮጵያ፡እንድ­ንገዛ፡ለቅዱስ፡ስምህ፡እንዲሆንም፡­ኑሮዋችን፡በሰላም፡በደኅና፡በዚህ፡­ዓመት።የዕለቱ፡መዝሙር። *”ሰአሉ፡ለነ፡ሐዋርያት፡አስራብ፡ዘወርቅ፡ወሐይዝተ፡ጽድቅ፡ወዘሐረገ፡ወይን፡አዕጹቅ፡ሰአሉ፡ለነ፡አስተምሕሩ”።ትርጉም፦የወርቅ፡ፏፏቴዎች፡የጽድቅ፡ፈሳሽና፡የወይን፡ሐረግ፡ቅርጫፎች፡ሐዋርያት፡ለምኑልን፡አማልዱን።አ­ባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በሰዓታቱ፡ላ­ይ። *”ሰላም፡ለምልኪ፡እምዐቢይተ፡ቁልዝም፡ዘኮነ።ዘሠናየ፡ልሕቀ፡ወዘአዳመ፡ተሐፅነ።እምእግዚአብሔር፡ከሀሊ፡ነሢኦ፡ሥልጣነ።በኃይለ፡ጸሎቱ፡ቀነየ፡ሰይጣነ።እንዘ፡ያፀውሮ፡ገብላተ፡ወስቑረ፡ዕብነ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም1። *የዕለቱ፡ዓራራይ፡ዜማ፦”አባ፡ዮሐንስ፡ባርከ፡ፍሬሃ፡ለምድር፡ቀዳማዌ፡ሣዕረ፡ደኃራዌ፡ሰብለ፡ዕተብ፡ወጸሊ፡ፍሬሃ፡ለምድር”። ትርጉም፦አባ፡ዮሐንስ፡የምድርን፡ፍሬዋን፡ባርክ፡፡መጀመሪያ፡ሳርን፡ሁለተኛም፡ሰብልን፡ባርክ፡ስለምድር፡ፍሬ፡ጸልይ። *የዕለቱ፡ምልጣን፡ግእዝ፡ዜማ፦”ወአንተኒ፡ሕጻን፡ነቢየ፡ልዑል፡ትሰመይ፡ዓርኩ፡ለመርዓዊ፡ትሰመይ፡ወአዝማዱ፡በሥጋ፡ትሰመይ፡ተፈኖከ፡ታርኁ፡አናቅጸ፡ጽድቅ”።ትርጉም ፦አንተም፡ሕጻን፡የልዑል፡ነቢይ፡ትባላለህ፡፡ለሙሽራው፡ሚዜ፡ትባላለህ፡የሥጋ፡ዘመዱ፡ትባላለህ፡የጽድቅ፡በሮች፡እንድተፍት፡ተልከሃል።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”አድኅነኒ­፡እምእለ፡ሮዱኒ፡እስመ፡ይኄይሉኒ።­ወአውፅአ፡እሞቅሕ፡ለነፍስየ።ከመ፡­እግነይ፡ለስምከ፡እግዚኦ”።መዝ141፥6-7፡ወይም፡መዝ64፥11-12።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ­11፥1-20።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡ቅ­ዳሴ፡ሐዋርያት፡ነው።መልካም፡አዲስ­፡ዓመትና፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን። ባርክ_ለነ ባርክ ለነ እግዚኦ ዘንተ ዓመተ ምሕረትከ በብዝኃ ኂሩትከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ ከመንግነይ ለስምከ ቅዱስ/2/ ወከመ ይኩን ንብረትነ በሰላም ወበዳኅና ለዝንቱ ዓመት/2/ ባርክልን አቤቱ ይህንን የምሕረት ዓመታችንን በቸርነትህ ብዛት ለሕዝቦችህ ኢትዮጵያ እንድንገዛ ለቅዱስ ስምህ /2/ እንዲሆንልን ኑሮአችን በሰላም በደኅና በዚህ ዓመት /2/ “ስዓትን በስዓት ቀንን በቀን […]

Continue reading

ዛሬ፡ጳጉሜን5፡ቀን

*እንኳን፡ከዐሥራ፡ሁለቱ፡ደቂቀ፡ነቢያት፡አንዱ፡ለሆነው፡ለታላቁ፡ነቢይ፡ለቅዱስ፡አሞጽ፡የዕረፍት፡በዓልና፡እናትና፡አባቱ፡የተውለትን፡ንብረት፡በመተው፡፡ከዓለም፡ለወጣ(ወደ፡ገዳም፡ለገባ)ከልብስ፡ተራቁቶ፡ለሚኖር፡በጸሎቱ፡ታላቁን፡አስፈሪ፡ዘንዶ፡ለማዳ፡እንስሳ፡ላደረገ፡ለታላቁ፡አባት፡ለብርቱ፡ልጅ፡አባ፡በርሱማ፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን፡፡በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከንጽሕ፡ከድግል፡አባት፡ከምስር፡አገር፡ኤጲስቆጶስ፡ከአባ፡ያዕቆብ፡ዕረፍትና፡ከታላቁ፡አባት፡ከአባ፡መግደር፡ዕረፍት፡ረድኤትና፡በረከትን፡ይደርብን። *”ሰአሉ፡ለነ፡ነቢያት፡ስኩራነ፡መንፈስ፡ምሉኣን፡ሞገስ፡አቅርንተ፡ሥሉስ፡ቅዱስ”።ትርጉም፦የሥላሴ፡ነጋሪቶች(ዐዋጅ፡ነጋሪዎች)፡የምትኾኑ፡ክብርን፡የተመላችኊ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡የተቃኛችኊ፡ነቢያት፡ለምኑልን፡ለእኛ፡አማልዱን።አ­ባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በሰዓታቱ፡ላ­ይ። *”ሰላም፡ለበርሱማ፡ትርሲተ፡ዓለም፡ዘገደፈ።እስከ፡ኢያጥረየ፡አሐደ፡ዐጽፈ።ወዲበ፡ዝኒ፡ወሰከ፡ፃማ፡ተጋድሎ፡ትረፈ።ከመ፡ያጽምዕ፡አመ፡ደኃሪ፡ምስለ፡ቅዱሳን፡ምዕራፈ።ማዕከ፡ሥጋሁ፡ወምድር፡ኢገብራ፡መንጸፈ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የጳጉሜን5። *የዕለቱ፡ምስባክ፦”ላዕለ፡ተኵላ፡ወከይሲ፡ትፄዐን።ወትከይድ፡አንበሳ፡ወከይሴ።እስመ፡ብየ፡ተወከለ፡አድኅኖ”።መዝ90፥13-14።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ5፥1-17፡ወይም፡ማር16፥15-19።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የሠለስቱ፡ምዕት፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Continue reading

ዛሬ፡ጳጉሜን4፡ቀን

*እንኳን፡ለታላቁ፡ለተጋዳይ፡አባት፡ለአባ፡ባይሞንና፡ለሮሜ፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡ሊባርዮስ፡ለዕረፍታቸው፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታቡ፦ከአባ፡ባይሞን፡ከስድስቱ፡ወንዱሞቹ፡መነኰሳት፡ሰማቸው፡ከዮሐንስ፣ከኢዮብ፣ከዮሴፍ፣ከላስልዮስ፣ከያዕቆብና፡አብርሃም፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን። *”ሰላም፡ዕብል፡በልሳንየ፡መዋቲ።፯ተ፡አኃወ፡ኅዱራነ፡በአት፡አሐቲ።ሶበ፡ፈቀደት፡እሞሙ፡ትርእዮሙ፡ይቤልዋ፡ላቲ።ኢትክሊ፡ትርአዪነ፡በዓለም፡ሰማይ፡እንታክቲ።ለእመ፡በዝየ፡ርኢክነ፡አንቲ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የጳጉሜን4። *የዕለቱ፡ዓራራይ፡ዜማ፦”ማዕረሩሰ፡ኀልቀተ፡ዓለም፡ውእቱ፡ወአፀዱኒ፡እሙንቱ፡መላእክት፡እምበለስ፡አእምሩ፡አምሳሊሁ፡እምከመ፡በጽሐ፡ጊዜሁ፡ይፌንዎሙ፡ለመላእክት፡በቃለ፡ቀርን”። ትርጉም፡- መከሩስ(ማ)የዓለም፡ፍጻሜ፡ነው፡አፃጆችም፡መላእክት፡ናቸው፡ምሳሌውን፡ከበለስ፡እወቁ(ተማሩ)ጊዜው፡በደረሰ፡ጊዜ፡መላእክትን፡በመለከት፡ቃል፡ይልካቸዋል፡፡ *መዝሙር፡ዘሰንበት(የዚህ፡ሳምንት፡መዝሙር)፦”ከመ፡እንተ፡መብረቅ፡ዘይወጽእ፡እምጽባሕ።ወያስተርኢ፡እስከ፡ዓረብ።ከማሁ፡ምጽአቱ፡ለወልደ፡እግዚአብሔር።ምስለ፡ኃይለ ሰማያት፡በንጥረ፡መባርቅት።ከመ፡እንተ፡መብረቅ፡ዘይወጽእ፡እምጽባሕ።ምስለ፡አእላፍ፡መላእክት፡ወኲሎሙ፡ሊቃነ፡መላእክት።ከመ፡እንተ፡መብረቅ፡ዘይወጽእ፡እምጽባሕ።አክሊለ፡አክሊላት፡ዲበ፡ርእሶሙ፡ለካህናት”።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ። *የዕለቱ­፡ምስባክ፦”እግዚአብሔር፡ገሃደ፡ይ­መጽእ።ወአምላክነሂ፡ኢያረምም።እሳ­ት፡ይነድድ፡ቅድሜሁ”።መዝ49፥2-­3።የሚነበው፡ወንጌል፡ማቴ17፥11­-37።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ያዕቆብ­፡ዘሥሩግ፡ነው።­መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን­።

Continue reading