ዛሬ፡መስከረም14፡ቀን (24 Sept 2018)

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።
          *ዛሬ፡መስከረም14፡ቀን
*እንኳን፡ለኢትዮጽያውያን፡ጻድቃን፡ለቀዳማዊው፡ንጉሥ፡ለዓምደ፡ጽዮን፡ልጅ፡ለነበሩና፡ድንጋዩን፡እንደ፡ጀልባ፡ተጠቅመው፡የጣናን፡ሐይቅ፡ለተሻገሩት፡ለታላቁ፡አባት፡አቡነ፡ያሳይ፡ዘማንዳባና፡እጆቻቸው፡እንደፋና፡እያበሩ፡ለጣና፡ሐይቅ፡ገዳማት፡በመብራትነት፡ያገለግሉ፡ለነበሩት፡ለፃህና፡መምህራን፡ለሆኑ፡አባቶች፡ዐሥራ፡አንደኛ፡ለሆነ፡ለፃና፡መምህር፡ለቅዱስ፡አባት፡ለአቡነ፡ጴጥሮስ፡ቀዳማዊ፡ለዕረፍታቸው፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ሃምሳ፡ዓመት፡በዓምድ፡ላይ፡ቆሞ፡ሲጸልይ፡ከኖረው፡አቡነ፡አጋቶን፡ዘአምድ፡ከዕረፍቱ፡በዓል፣ከቀሲስ፡ዴግና፡ዕረፍት፣ከሰማዕት፡መቃራ፣ከበርተሎሜዎስ፡ከአውዳራና፡ከናሶን፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*አቡነ፡ጴጥሮስ፡ቀዳማዊ፡-ትውልድ፡ሀገራቸው፡ሸዋ፡ቡልጋ፡ልዩ፡ስሙ፡ደብረ፡ጽላልሽ፡ነው፡፡ጻድቁ፡በዐፄ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ዘመን፡ለ48፡ዓመታት፡የቅዱስ፡ገላውዲዮስን፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ሲያጥኑ፡ኖረዋል፡፡ከተሰዓቱ፡ቅዱሳን፡አንዱ፡የሆኑት፡አቡነ፡ሊቃኖስ፡እጆቻቸው፡እያበሩ፡ለገዳሙ፡መብራትነት፡ይጠቀሙባቸው፡እንደነበረው፡ሁሉ፡የአቡነ፡ጴጥሮስ ቀዳማዊም፡እጆቻቸው፡እንደፋና፡እያበራ፡ለጣና፡ሐይቅ፡ገዳማት፡በመብራትነት፡ያገለግል፡ነበር፡፡ጻድቁ፡ለ31፡ዓመታት፡ከመላእክት፡ጋር፡እየተነጋገሩ፡የኖሩ፡ሲሆን፡መናም፡ከሰማይ፡እያወረዱ፡መነኮሳቱን፡ይመግቡ፡ነበር፡፡ድውያንን፡በመፈወስ፣ ሙታንን፡በመንሣት፡ብዙ፡አስተደናቂ፡ተአምራት፡እያደረጉ፡ወንጌልን፡በሀገራችን፡ዞረው፡በማስተማር፡እግዚብሔርን፡ሲያገለግሉ፡ኖረው፡በዚህች፡ዕለት፡በሰላም፡ዐርፈው፡ቅድስት፡ነፍሳቸውን፡ቅዱሳን፡መላእክት፡በክብር፡ተቀብለዋታል፡፡ምንጭ፡መዝገበ፡ቅዱሳንና፡ስንክሳር።
*”ሰላም፡ለአጋቶን፡አክሊለ፡ወሞገሳ።ሀገረ፡ተንሳ።በብዙኅ፡ጻሕቅ፡ለመግሥተ፡ሰማይ፡እንዘ፡የኃሥሣ።፡ፃመወ፡ዓመታተ፡እስራ፡ወሠላሳ።ወበላዕለ፡ዓምድ፡አዝማናተ፡ኃምሳ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም14።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወወሀብኮሙ፡ትእምርተ፡ለእለ፡ይፈርሁከ።ከመ፡ያምሥጡ፡እምገጸ፡ቅስት።ወይድኀኑ፡ፍቁራኒከ”።መዝ59፥9-10።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ14፥22-36።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Comments are closed.