ዛሬ፡መስከረም9፡ቀን (Sept 19 2018)

*እንኳን፡በሮሜ፡አገር፡ፍሩምያ፡በምትባል፡ከተማ፡በመላእክት፡አለቃ፡በቅዱስ፡ሚካኤል፡በስሙ፡በተሰራ፡ቤተ፡ክረስቲያን፡ላደረገው፡ተአምር፡መታሰቢያ፡በዓልና፡ከኀላፊው፡ከዚህ፡ዓለም፡መንግሥቱ፡መንኖ፡ተጋድሎውን፡በዛፍ፡ላይ፡ሁኖ፡ለፈጸመ፤የደረቀውን፡ግንድ፡ላለመለ፣ለጽጌ፣ለፍሬ፡ለአደረሰ፡ላሳየ፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ላሰኘ፡ለንጉሥ፡ያሳይ፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦መጺል፡ከምትባል፡አገር፡ኤጲስቆጶስ፡ከቅዱስ፡አባት፡ከአባ፡ቢሶራ፡በሰማዕትነት፡ከዐረፈ፣ከቅዱስ፡ፋሲለደስ፡ጋር፡ዐሥራ፡አራት፡ሺህ፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ወንዶችና፡ሰባት፡ሴቶችም፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለአባ፡ያሳይ፡ብእሴ፡ሰማይ፤ለአምላኩ፡ቀናኢ፤ሐራይ፡መዋኢ”።ትርጉም፦ድል፡ነሺ፡ጭፍራ፡ለአምላኩ፡ቀናተኛ፡የሰማይ፡ሰው፡ለኾነ፡ለአባ፡ያሳይ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ።
*”ሰላም፡ለያሳይ፡እምነ፡መንግሥቱ፡ዘተድህለ።መንግሥተ፡ሰማያት፡ያድምዕ፡ወዘኢየኀልፍ፡ብዕለ።ውስተ፡ጉንደ፡ዕፅ፡ይቡስ፡አመ፡ተለዓለ።በትሩፋቲሁ፡ከመ፡ያርኢ፡ኃይለ።አሥረፀ፡ሶቤሃ፡ወአወጽአ፡ቔጽለ”።ትርጉም፦የማያልፍ፡ሀብትንና፡መንግሥተ፡ሰማያትን፡ያገኘ፡ዘንድ፡ከምድራዊው፡መንግሥቱ፡የኰበለለ፡ለኾነ፡ለያሳይ፡ሰላምታ፡ይገባል፤በትሩፋቱ፡ኃይልን፡ያሳይ፡ዘንድ፡በደረቀ፡ዕንጨት፡ግንድ፡ላይ፡በወጣ፡ጊዜ፡በዚያን፡ጊዜ፡ቅጠሎችን፡አውጥቶ፡ለመለመ።
*”ሰላም፡እብል፡ለዓቢይ፡መንክሩ።ዘተክሥተ፡ዮም፡በውስተ፡ዳቤሩ።ፈለገ፡ማይ፡ይሚጡ፡እንዘ፡ይመክሩ።ተሠጥቀ፡ኰኵሕ፡እንተ፡ዐላውያን፡አንበሩ።ሶበ፡ሚካኤል፡ዘበጦ፡በበትሩ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም9
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ደምፁ፡ወተሐምጉ፡ማያቲሆሙ።ወአድለቅለቁ፡አድባር፡እምኃይሉ።ፈለግ፡ዘይውኅዝ፡ያስተፌሥሕ፡ሀገር፡እግዚአብሔር”።መዝ45፥3-4።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ7፥24-29።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ያዕቆብ­፡ዘሥሩግ፡ነው።­መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን­።

Comments are closed.