ዛሬ፡መስከረም12፡ቀን (22 Sept 2018)

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።
*ዛሬ፡መስከረም12፡ቀን
*እንኳን፡ለሊቀ፡መላእክት፡ለቅዱስ፡ሚካኤል፡እግዚአብሔር፡ወደ፡አሞፅ፡ልጅ፡ወደ፡ነቢዩ፡ኢሳይያስ፡ለንጉሱ፡ሕዝቅያስ፡ከደዌው፡እንዳዳነው፡በእድሜው፡ላይ፡አስራ፡አምስት፡አመት፡እንደተጨመረለት፡ንገረው፡ብሎ፡ለተላከበት፡ለወራዊ፡መታሰብያ፡በዓልና፡በኤፌሶን፡ሀገር፡በ431ዓ.ም(ሦስተኛው፡ጉባኤ)ሁለት፡መቶ፡ኤጲስ፡ቆጶሳት፡ንስጥሮስን፡ለማውገዝ፡ለተሰበሰቡበት፡ቀን፡ለመታሰቢያ፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከሰማዕት፡አፍላሆስ፡ከመታሰቢያውና፡ከሥጋው፡ፍልሰት፣ከእስክድርያ፡አገር፡ከሆኑ፡ከባልንጀሮቹ፡ሰማዕታትም፡ከመታሰቢያቸው፣ከሰማዕታት፡ከሉዩራስና፡ባሌኒኮስ፣ከቅዱስ፡ኢያቄምና፡ከቅድስት፡ሐናም፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለ፪፻፡ኤጲስ፡ቆጶሳት፡እለ፡ተጋብኡ፡በኤፌሶን፡ሀገር፤ወአጽንኡ፡ሃይማኖተ፡በእግዚአብሔር”።ትርጉም፦በኤፌሶን፡ሀገር፡ተሰብስበው፡ሃይማኖትን፡በእግዚአብሔር፡የጸኑ፡ለኾኑ፡ለኹለት፡መቶው፡ኤጲስ፡ቆጶሳት፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ።
*”ሰላም፡ለክሙ፡ሐራ፡ክረስቶስ፡መድኅን።ጥዑማነ፡ዜና፡ወዝክር፡እምአስካለ፡ወይን።ርእሰ፡ንስጥሮስ፡ትምትሩ፡በሰይፈ፡ሃይማኖት፡ርሱን።ዘተጋባእክሙ፡ሀገረ፡ኤፌሶን።ክልኤቱ፡ምዕት፡ጳጳሳት፡ኄራን”።ትርጉም፦በጋለ፡የሃይማኖት፡ሰይፍ፡የንስጥሮስን፡ራስ፡ትቆርጡ፡ዘንድ፡በኤፌሶን፡ሀገር፡የተሰበሰባችኊ፡የኾናችኊ፡ደጋጎች(የተመረጣችሁ)ኹለት፡መቶ፡ሊቃውንት፡ዜናችኹና፡መታሰቢያችኊ፡ከወይን፡ፍሬ፡ይልቅ፡የጣፈጠ፡የመድኅን፡ክርስቶስ፡ጭፍራ፡ሰላምታ፡ለእናንተ፡ይገባል።
*”ሰላም፡ለምቅወምከ፡ዘልዑል፡ማዕረጋ።እምቅዋመ፡አእላፍ፡እንግልጋ።ሚካኤል፡መንፈስ፡ዘንበለ፡ሥጋ።ታድኅን፡ዘተመንደበ፡ለማዕበለ፡ባሕር፡እምጹጋ፡ወለእለ፡በበድው፡ትባልሕ፡በጸጋ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም12።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ይትዐየን፡መልአከ፡እግዚአብሔር፡ዐውዶሙ።ለእለ፡ይፈርህዎ፡ወያድኅኖሙ።ጠዐሙ፡ወታእሙሩ፡ከመ፡ኄር፡እግዚአብሔር።”መዝ33፥7-8።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ18፥15-19።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ቄርሎስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Comments are closed.