ወደ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሎንዶን እንኳን ደህና መጣችሁ
- ደብራችን ደብረብስራት ቅዱስ ገብርኤል ከተመሰረተች ጥቂት አመታት ያስቆጠረች ስትሆን በነዚህ አመታት ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የአገልግሎት ዘርፏንም ሆነ የምዕመናንን ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ በማሳደግ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።
- ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በሰሜን ምዕራብ ለንደን አማካይ ቦታ ላይ የምትገኝ ሲሆን አመቺ የሆነ የትራንስፖርት መዳረሻ ጭምር ናት። ከላይ እንደገለፅነው በአሁኑ ጊዜ የአገልግልት ዘርፋችንን በይበልጥ ለማሳደግም ሆነ ለማጠናከር ብሎም የተዋህዶ ልጆች በያሉበት ቦታ ሆነው የአገልግሎት ተሳታፊያችን ይሆኑ ዘንድ በማሰብ ይህንን ድረገጽ አዘጋጅተናል።
- ስለሆነም በየጊዜው በድረ ገጻችን ላይ በምንለጥፋቸው መንፈሳዊ መልዕክቶች መንፈሳዊ ህይወትዎን እንዲያጎለብቱ እየጋበዝን፤ ለድረ ገጻችን ማደግ በየጊዜው ከምዕመናን የምናገኛቸው አስተያየቶች ጠቃሚ በመሆናቸው እርስዎም የበኩልዎን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እንጠይቃለን።
- በመጨረሻም በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ምዕመናን የሚሆኑ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችንና መረጃዎችን ስለምንለጥፍ በድጋሚ መጥተው እንዲጎበኙን እንጋብዛለን።
- እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ!!