ዛሬ፡መስከረም16፡ቀን (Sept 26 2018)

*”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።
        *ዛሬ፡መስከረም16፡ቀን
*እንኳን፡ከጌታችን፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡መቃብር፡ላይ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ለታነፀችበትና፡ለተቀደሰችበት፡በዓል፣በኢየሩሳሌም፡አገር፡ንግሥት፡ዕሌኒ፡የገለጠቻቸው፡የከበሩ፡ቦታዎች፡ሁሉ፡ለተሠሩበትና፡ለከበሩበት፡በዓል(ለደመራ፡በዓል)፣በፋርስ፡ንጉሥ፡አሜኔሶር፡እጅ፡ተማርኮ፡ወደ፡ነነዌ፡አገር፡ለተወሰደ፡ከንፍታሌም፡ነገድ፡ለሆነ፡ለገባኤል፡ልጅ፡ለቅዱስ፡ጦቢት፡የዕረፍት፡በዓልና፡ተርታ፡ነገርንም፡እንዳይናገር፡ደንጊያ፡ጎርሶ፡ለኖረ፡ለታላቁ፡አባት፡ለአባ፡አጋቶን፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከቅዱሳን፡ከወርቅላ፣ከስምዖን፣ከመርቄኖስ፣ከሐሊ፡ከሮቂኖስ፣ከሉክያኖስ፣ከአርዝማኖስ፣ከጴጥሮስ፡ከሐና፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*አባ፡አጋቶን፦ወደ፡ቲቤያድ፡ገዳም፡ሲመጣ፡ገና፡ሕፃን፡ነበር።ያሳደገው፡ያስተማረው፡አባ፡ጴማን፡ነው።በመቀጠልም፡ወደ፡አስቄጥስ፡ተጉዞ፡ከአባ፡እስክድር፡እና፡ዞይለስ፡ጋር፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ኖሯል።ገዳመ፡አስቄጥስ፡ለመጀመርያ፡ጊዜ፡ሲጠፋ፡አባ፡አጋቶን፡ከደቀ፡መዝሙሩ፡ከአባ፡አብርሃም፡ጋር፡በመሆን፡ከደብረ፡ትሮኤ፡ሳይርቅ፡ከዓባይ፡ወንዝ፡አጠገብ፡መኖር፡ጀመረ።
*አንድ፡ጊዜ፡ስለ፡አባ፡አጋቶን፡ትኅትና፡የሰሙ፡መነኰሳት፡ሊያዩት፡መጡ።የቁጣ፡ስሜቱን፡ወተውንና፡አለመተውን፡ለማረጋገጥ፡ብለው”አመንዝራውና፡ትዕቢተኛው፡አጋቶን፡ማለት፡አንተ፡ነህ?”አሉት።አባ፡አጋቶንም”አዎ፡ትክክል፡ነው”፡አላቸው።ቀጥለውም”ፍሬ፡የሌለው፡ነገር፡ዘወትር፡የምታወራ፡አጋቶን፡ማለት፡አንተ፡ነህ?”አሉት”አዎ፡ነኝ፡አላቸው።”መናፍቅ፡አጋቶን፡ማለት፡አንተ፡አይደለህምን?”ሲሉ፡ጠየቁት፡ያን፡ጊዜ፡ግን”መናፍቅስ፡አይደለሁም”ሲል፡መለሰላቸው።በዚህ፡ጊዜ”እስካሁን፡የተናገርንብህን፡ሁሉ፡ተቀብለህ፡የመጨረሻውን፡ለምን፡ተቃወምክ?”አሉት።አባ፡አጋቶንም”የመጀመሪያያዎቹን፡ወቀሳዎች፡ለነፍሴ፡ተስማሚዎች፡ናቸውና፡ተቀበልኳቸው።ኑፋቄ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡መለየት፡ነው፡እናም፡እኔ፡ከፈጣርዬ፡መለየት፡አልፈልግም፡አላቸው”።በዚህ፡የተነሣም፡የርሱ፡ሕይወት፡አስደነቃቸው።
አንድ፡ቀን፡አባ፡አጋቶን፡በእጁ፡የሠራቸውን፡ነገሮች፡ለመሸጥ፡ወደ፡ገበያ፡ሲወጣ፡በመንገድ፡ዳር፡አንድ፡ሽባ፡ሰው፡አገኘ።ሽባውም፡የት፡እንደሚሄድ፡አባ፡አጋቶንን፡ጠየቀው።”አንዳንድ፡ነገሮች፡ለመሸጥ፡ወደ፡ገበያ፡እሔዳለው”አለው።ሽባው፡ሰውም”እባክህ፡ተሸከምህ፡ወደዚያ፡ውሰደኝ”ሲል፡ለመነው።አባ፡አጋቶንም፡ያንን፡ሰው፡ተሸክሞ፡ወደ፡ከተማ፡ወሰደው።ሽባው፡ሸውዬ”ዕቃዎችን፡ከምትሸጥበት፡ቦታ፡አጠገብ፡አኑረኝ”፡አለው።አባ፡አጋቶንም፡እንደዚያው፡አደረገው።አባ፡አጋቶን፡የመጀመርያውን፡ዕቃ፡ሲሸጥ”ምን፡ያህል፡ሸጥከው?”ብሎ፡ሽባው፡ሰው፡ጠየቀው።እርሱም፡ዋጋውን፡ነገረው።ያም፡ሽባ፡ሰው”እባክህ፡ዳቦ፡ግዛልኝ”ሲል፡ለመነውና፡ገዛለት።አባ፡አጋቶን፡ሁለተኛው፡ዕቃ፡ሲሸጥ”ምን፡ያህል፡ሸጥከው”ሲል፡ያሰው፡ጠየቀው።እርሱም፡ዋጋው፡ነገረው”እባክህ፡ይህን፡ነገር፡ግዛልኝ”ሲል፡ለመነው።አባ፡አጋቶንም፡ገዛለት።በዚህም፡መልኩ፡ሁሉንም፡ዕቃዎች፡ሸጦ፡በጨረሰ፡ጊዜ፡ያሽባ፡ሰው፡ወደ፡በዓትህ፡ትመለሳለህን?”ሲል፡ጠየቀው”አዎ”እንግደውስ፡እባክ፡ቀድሞ፡ወደአገኸኝ፡ስፋራ፡አዝለህ፡መልሰኝ”፡አለው።አባ፡አጋቶንም፡ያን፡ሽባ፡ሰው፡ተሸክሞ፡ወደ፡ቀድሞ፡ቦታው፡መለሰው።በዚህ፡ጊዜ፡ሽባው፡ሰው”አባ፡አጋቶን፡በሰማይና፡በምድር፡በረከት፡ተሞላህ”ብሎ፡ተናገረው።ወድያው፡አባ፡አጋቶን፡አይኑን፡አንስቶ፡ሽባው፡ቢያየው፡በቦታው፡የለም።ሊፈትነው፡ይህን፡ያደረገው፡መልአከ፡እግዚአብሔር፡ነበር።ምንጭ፦በበረሐው፡ጉያ፡ውስጥ፡ከሚለው፡መጽሐፍ፡ዲያቆን፡ዳንኤል፡ክብረት፡ከጻፈው።
*”ሰላም፡ለጦቢት፡መፍቀሬ፡ምጽዋት፡ዘተብህለ።እስመ፡ይገብር፡ምጽዋተ፡ወብዙኀ፡ሣህለ።እንዘ፡ምስለ፡ሕዝቡ፡ይሄሉ፡ሀገረ፡ነነዌ፡ማዕከለ።እምከመ፡ረከበ፡በእሴ፡ቅቱለ።እንበለ፡ይትብሮ፡ኢይጥዕም፡እከለ።”አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም16።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”እቤ፡አዐቅብ፡አፉየ፡ከመ፡ኢይስሐት፡በልሳንየ።ወአንቀርኩ፡ዐቃቤ፡ለአፋየ።ሶበ፡ይትቃወሙኒ፡ኀጥአን፡ቅድሜየ”።መዝ38፥1፡ወይም፡መዝ50፥18-19።የሚነበበው፡ወንጌል9፥1-12፡ወይም፡ዮሐ10፥22-42።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡ቅዳሴ፡እግዚእነ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

Comments are closed.