ዛሬ፡መስከረም10፡ቀን

“በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።

*እንኳን፡ለእመቤታች፡ለቅድስት፡ድንግል፡ማርያም፡በፄዴንያ፡አገር፡በማርታ፡ቤት፡ሥጋ፡የለበሠች፡ከምትመስል፡ከእመቤታች፡ሥዕል፡ከሠሌዳዋ፡ቅባት፡እየተንጠፈጠፈ፡ተአምር፡ለሠራችበት፡ቀን፡መታሰብያ፡በዓልና፡የጌታችን፡የአምላካችን፡የመድኃኒታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡­ቅዱስ፡መስቀል፡ወደ፡አገራችን፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ለገባበት(ተቀጽል፡ጽጌ)አፄ፡መስቀል)ቀን፡ለመታሰቢያ፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪም፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦አምላክን፡የወለደች፡የእመቤታችን፡የቅድስት፡ድንግል፡ማርያም፡የተወለደችበት፡ነው፡የሚሉ፡አሉ።(ይህም፡የአስቄጥስ፡ገዳም፡የከበረ፡አባ፡መቃርስ፡በጻፈው፡መጽሐፈ፡ግጻዌ፡ተጽፎል፡እንዲሁም፡ደግሞ፡በላዕላይ፡ግብጽ፡በሚገኝ፡መጽሐፈ፡ግጻዌ፡የከበረች፡ድንግል፡እመቤታችን፡የከበረች፡ሐና፡በታኅሣሥ፡ወር፡በዐሥራ፡ሰባት፡እንደፀነሰቻትና፡መስከም፡በዐሥር፡ቀን፡እንደወለደቻት፡ተጽፍአል)፣ከከሀዲው፡ሆሎፎርኒስ፡እጅ፡በጥበቧ፡እስራኤልን፡ካዳነቻቸው፡ከጥበበኛ፡ከከበረች፡ከዮዲት፡በዓለ፡ዕረፍትና፡ከከበረች፡ሰማዕት፡ቅድስት፡መጥሮንያ፡ዕረፍት፣ከቅድስት፡አትናስያና፡ሦስት፡ልጆቿ፡ከመታሰቢያቸው፡በረከትና፡ረድኤትን፡ያሳትፈን።
“መስቀል፡­ጒድበ፡ሙስና፡ዲበ፡ሰይጣን፡ወሰይፈ­፡ሙቃየ፡አርእስቲሆሙ፡ለአጋንንት፤መስቀል፡ረምኃ፡እሳት፡ዘይረግዞሙ፡ለመናፍስት፡ርኵሳን፤ወሐፀ፡መብረቅ፡ዘይደጒፆሙ፡ለሠራዊተ፡መስቴማ።መስቀል፡ፀወን፡ዘኢይክል፡በጺሐ፡ኀቤሁ፡ዘኢነሥአ፡ማኅተመ፡ሥላሴ።መስቀል፡ወልታ፡ጽድቅ፡ዘእምየማን፡ወእም፡ጸጋም።መስቀል፡ንዋየ፡ሐቅል፡ለፀብዕ፡በከመ፡ይቤ፡ጳውሎስ፡ሐዋርያ፡እስመ፡ቀትልክሙ፡ኢኮነ፡ምስለ፡ዘሥጋ፡ወደም።መስቀል፡ጽርዐ፡ሃይማኖት፡ዘኢይክል፡ሰጢጦቶ፡ሥጽረተ፡ሐፀ፡ወኢደርብዮቶ፡ኵያንው፡ወአርማኅ።መስቀል፡ዘገብረ፡በአምሳሊሁ፡ለእደ፡ሙሴ፡በገዳም፡ራፊድ፡በእንተ፡ፀብዐ፡አማሌቅ።መስቀል፡ዘአጥዐሞ፡ለማይ፡መሪር፡በገዳም፡ሱር፡ሶበ፡ተወድየ፡ውስቴቱ፡በእደ፡ሙሴ።መስቀል፡ማኅተመ፡ቅድስና፡ወንጽሕ።መስቀል፡አክሊለ፡መዊዕ፡ዘመስተጋድላን፡ወሠርጎ፡ትርሲት፡ለእለ፡ተዓሥሩ፡ውስተ፡መርዐ፡በግዑ።መስቀል፡ነቅዕ፡ዘኢይነጽፍ፡ወአዘቅተ፡ክብር፡ዘምሉዕ፡ረባሐ”።­ትርጉም፦መስቀል፡ሰይጣንን፡የሚያ­ጠፋ፡ምሳር፡ነው፤የአጋንንትንም፡ራ­ሶች፡የሚቆርጥ፡ሰይፍ፡ነው፤መስቀል፡ርኩሳን፡መናፍስትን፡የሚወጋቸው፡የእሳት፡ዘገር፡ነው፤የአመስቴማውያንንም(የጠላት፣የከሳሽ፡የጠበኛ)ሠራዊት፡የሚመታ፡የመብረቅ፡ጦር፡ነው።መስቀል፡ማኅተመ፡ሥላሴ(የሥላሴ፡ልጅነት)የሌለው፡ሰው፡ወደእርሱ፡ሊቀርበው፡የማይቻለው፡አምባ፡መጠጊያ፡ነው።መስቀል፡ከግራ፡ከቀኝም፡ለሚመጣ(ጠላት)የጽድቅ፡ጋሻ፡ነው።ጳውሎስ”ውጊያችሁ፡ከሥጋና፡ከደም፡ጋር፡አይደለም”እንዳለው፡መስቀል፡የጦር፡መሣርያ፡ነው።መስቀል፡የጦር፡ውጋት፡ሊቀድደው፤የቀስትና፡የዘንግም፡ጫፍ፡ሊበሳው፡የማይችል፡የሃይማኖት፡ጥሩር፡ነው።መስቀል፡አማሌቃውያንን፡ለመውጋት፡በራፊድ፡በረሐ፡በዘረጋው፡በሙሴ፡እጅ፡አምሳል፡የተሠራ፡ነው።መስቀል፡በሙሴ፡እጅ፡ወደ፡ውስጥ፡በተጨመረ፡ጊዜ፡መራራውን፡ውኃ፡በሱር፡በረሐ፡ያጣፈጠ፡ነው።መስቀል፡የቅድስናና፡የንጽሕና፡ማኅተም፡ነው።መስቀል፡ለሚጋደሉ፡የድል፡አክሊል፤ወደ፡በጉ፡ሰርግ፡ለተጠሩትም፡የሰርግ፡ልብሳቸው፡ነው።መስቀል፡የማይነጥፍ፡ምንጭ፤በቁዔትም(ጥቅምም)፡የሞላበት፡የክብር፡ጉድጓድ፡ነው።አባ፡ጊ­ዮርጊስ፡ዘጋሥጫ፡በውዳሴ፡መስቀል፡­ላይ1፥3።
“ሰላም፡ለሥዕልኪ፡ሀፈ፡ማኅየዌ።በፄዴንያ፡ወኢትዮጵያ፡በአውኀዘት፡በኢሕሳዌ።ለመፀብሐዊ፡ማቴዎስ፡ማርያም፡እንተ፡ረሰይኪዮ፡ወንጌላዌ።ይኩነነ፡ወትረ፡ፀሎትኪ፡እምዘመነ፡ኵሉ፡ምንሳዌ።ዓቃቤ፡ዘመዓልት፡ወዘሌሊት፡ሀላዌ”።መልክአ፡ሥዕል።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ወትቀውም፡ንግሥት፡በየማንከ።በአልባሰ፡ወርቅ፡ዑፅፍት፡ወኁብርት።ስምዒ፡ወለትየ፡ወርእዪ፡ወአፅምዒ፡እዝነኪ።”መዝ44፥9-10።የሚነበበው፡ወንጌል፡ሉቃ1፥46-57፡ወይም፡ማቴ25፥1-14።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የእመቤታች፡ማርያም፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንል።

Comments are closed.