ዛሬ፡መስከረም15፡ቀን (25 Sept 2018)

 
 *”በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ፡አሐዱ፡አምላክ፡አሜን”።
         *ዛሬ፡መስከረም15፡ቀን
*እንኳን፡ለኢትዮያዊው፡ጻድቅ፡ማኅሌተ፡ጽጌ፡ከአባ፡ጽጌ፡ድንግል፡ጋር፡በአንድነት፡እንደ፡አንድ፡ልብ መካሪ፡እንደ፡አንድ፡ቃል፡ተናጋሪ፡በመሆን፡ለደረሱት፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡ገብረ፡ማርያም፡ዘደብረ፡ሐንታ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለዲያቆናት፡አለቃ፡ለቀዳሜ፡ሰማዕት፡ለቅዱስ፡እስጢፋኖስ፡ለሥጋው፡ፍልሰት፡ለመታሰብያ፡ቀን፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ጠራው፡ከሚባል፡አገር፡እግራቸው፡በውኃው፡ሳይርስ፡በእግራቸው፡በባሕር፡ላይ፡ሲራመዱ፡ከነበሩት፡ከከበረ፡ፃድቅ፡ከአባ፡ጴጥሮስ፡በዓለ፡ዕረፍት፡ረድኤት፡በረከት፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለፍልሰተ፡ሥጋከ፡ዘተረክበ፡እምተከብቶ።አመ፡፲ወ፭፡ለወርኅ፡መስከረም፡ቲቶ።ተወኪፈከ፡እስጢፋኖስ፡መሥዋዕተ፡ሰላምየ፡በኢያስትቶ።ምስሌየ፡ግበር፡እግዚኦ፡ለሠናይቲከ፡ትእምርቶ።ናሁ፡ለውዳሴከ፡ርኢኩ፡ማኅለቅቆ”።ትርጉም፡ቅዱስ፡እስጢፋኖስ፡ሆይ!ቲቶ፡በሚባል፡መስከረም15፡ቀን፡ከተቀበረበት፡ለተገኘ፡ለሥጋህ፡ፍልሰት፡ሰላምታ፡ይገባል።ጌታዬ፡ባለማቃለልም፡የሰላሜን፡መሥዋዕት፡ተቀብለህ፡የበጎነትህን፡ምልክት፡ከእኔ፡ጋር፡አድርግ።የምስጋናህንም፡ፍጻሜ፡እነሆ፡አይቻለሁ።መልክአ፡ቅዱስ፡እስጢፋኖስ።
*”ሰላም፡እብል፡ለጴጥሮስ፡ብሕትወ።ኮከበ፡ጠራው።ወውስተ፡ዓለም፡ኅሩም፡እምበሊዐ፡ኅብስት፡ወጼው።እስከ፡አስተርአየ፡በአምሳለ፡ምትሐት፡ሕስው።ተሴስዮ፡ሣዕር፡አብደረ፡በበድው”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም15።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ብፁዕ፡ዘኀረይኮ፡ወዘተወከፍኮ።ወዘአኀደርኮ፡ውስተ፡አዕፃዲከ።ጸገብነ፡እግዚኦ፡እምበረከተ፡ቤትከ”።መዝ64፥4።የሚነበበው፡ወንጌል፡ሉቃ10፥30-38።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዮሐንስ፡ወልደ፡ነጎድጓድ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።

Comments are closed.