ዛሬ፡መስከረም7፡ቀን (Sept 17 2018)

*እንኳን፡ስለ፡ተዋሕዶ፡ሃይማኖት፡በአርዮሳዊያን፡ጢሙን፡ለተነጨና፡ጥርሱንም፡ለተነቀለ፡ለታላቁ፡ሊቅ፡ለእስክድርያ፡ሃያ፡አምስተኛ፡ኤጴስቆጶስ፡ለአቡነ፡ዲዮስቆሮስ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለእመቤታችን፡እናት፡ለቅድስት፡ሐና፡የልደቷ፡በዓል፡መታሰቢያ፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከመጥምቀ፡መለኮት፡እናት፡ከቅድስት፡ኤልሳቤጥ፡ከመታሰቢያዋ፣ከገቡላ፡ኤጴስቆጶስ፡ከከበረ፡አባት፡ከአባ፡ሳዊርያኖስ፡ዕረፍት፣ከከበሩ፡አጋቶንና፡ጴጥሮስ፡ከዮሐንስና፡ከአሞን፡ከእናታቸው፡ራፈቃ፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፣ከቅዱስ፡ፋሲለደስ፡ጋር፡በሰማዕትነት፡ከዐረፉ፡ከሁለት፡ሺህ፡ሰዎች፣ከጋንግራ፡ሰው፡ዳሳ፣ከአንጾኪያ፡ኤጲስቆጶስ፡ከናውላ፣ከመነኵሴውም፡ከጴጥሮስ፡ከመታሰቢያቸው፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለዲዮስቆሮስ፡ዘተመልኀ፡ጥረሲሁ፤ወተነጽየ፡ጽሕሙ፡ለክርስቶስ፡በእንተ፡ስሙ”።ትርጉም፦በክርስቶ፡ስም(ስለክርስቶስ፡ስም)ጢሙን፡የተነጨ፤ጥርሱንም፡የተነቀለ፡ለኾነ፡ለዲዮስቆሮስ፡ሰላምታ፡ይገባል።
*”ሰላም፡ለሐና፡እንተ፡ወለደታ፡ለማርያም፡ዘኮነት፡ተንከተመ፡ጽድቅ፡በኵሉ፡ዓለም፤ድንግል፡ወእም፤ወላዲቱ፡ለፀሓይ፡ዳግሚት፡ሰማይ”።ትርጉም፦ፀሓይን፡የወለደችው፡ኹለተኛዪቱ፡ሰማይ፤ድንግልም፡እናትም፤ለዓለሙ፡ኹሉ፡የእውነት፡ድልድይ(መሸጋገሪያ)የኾነችዪቱን፡ማርያምን፡ለወለደቻት፡ለሐና፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ።
*”ሰላም፡ለዲዮስቆሮስ፡ሃይማኖተ፡ንጉሥ፡ዘተሣለቀ።ተዋሕዶተ፡አምላክ፡ወሰብእ፡አመ፡ለክልኤ፡ነፈቀ።ያስተጻንዕ፡ህየ፡እለ፡ሀለዉ፡ደቂቀ።ዘተነጽየ፡እምነ፡ጽሕሙ፡ወእምአስናኒሁ፡ዘወድቀ።ፍሬ፡ሃይማኖቱ፡ፈነወ፡ብሔረ፡ርኁቀ”።ትርጉም፦ሰው፡የኾነ፡የአምላክን፡ተዋሕዶ፡ለኹለት፡በከፈለ፡ጊዜ፡በንጉሥ፡ሃይማኖት፡ላይ፡የተሣለቀ፡ለኾነ፡ለዲዮስቆሮስ፡ሰላምታ፡ይገባል፤በዚያ፡ያሉትን፡ልጆች፡ያጽናና፡ዘንድ፡ከወደቁ፡ጥርሶቹ፡ከተነጨ፡ጽሕሙ፡የሃይማኖት፡ፍሬ፡አድርጎ፡ወደ፡ሩቅ፡ሀገሩ፡ላከ።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም7።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”እስመ፡መምህረ፡ሕግ፡ይሁብ፡በረከተ።ወየሐውር፡እምኀይል፡ውስተ፡ኃይል።ወያስተርኢ፡አምላከ፡አማልክት፡በጽዮን”።መዝ83፥6-7።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማር1፥23-29።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የእመቤታች፡ማርያም፡ቅዳሴ­፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁ­ላችንም፡ይሁንልን።