ዛሬ፡መስከረም8፡ቀን (Sept 18 2018)

*እንኳን፡ለእግዚአብሔ፡ሰው፡ለሆነ፡ለየዋሁ፡ለቅኑ፡ለጻድቁ፡ለነቢያት፡አለቃ፡ለቅዱስ፡ሙሴ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለመጥምቀ፡መለኮት፡ለቅዱስ፡ዮሐንስ፡አባት፡ለበራክዩ፡ልጅ፡ለካህንና፡ለነቢዩ፡ለሆነ፡ለከበረ፡ለቅዱስ፡ዘካርያስ፡በንጉሥ፡ሄሮድስ፡እጅ፡ሰማዕትነት፡ለተቀበለበት፡ለዕረፍቱ፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከከበረ፡ዲማድዮስ፡ከግብጽ፡ደቡብ፡ደንጡ፡ከሚባ፡አውራጃ፡በሰማዕትነት፡ከዐረፈ፣ምግቡ፡የአጋዝን፡ወተት፡ከሆነ፡በዕረፍቱም፡ጊዜ፡ብዙ፡ተአምራትን፡ከአደረገ፡ከከበረ፡ከገዳማዊ፡ከቅዱስ፡ቂርቆስ፡ዕረፍት፣ከሰማዕቱ፡ሉክዮስ፡ከመታሰቢያው፣ከቅዱስ፡ኤርምያስና፡ከቅዱስ፡ዮሐንስ፣ከቅዱስ፡አንዲዎና፣ከቅዱስ፡ኤልያኖስና፡ከመነኰስ፡አሞንም፡ከመታሰቢያቸወ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለሙሴ፡ሊቀ፡ነቢያት፡ዘርእየ፡ሱራኄሁ፡ለጸባኦት፤ዘተመጠወ፡እምእደዊሁ፡ኦሪተ፡በጾም፡ወበጸሎት“።ትርጉም፦የሰራዊት፡ጌታን፡የብርሃን፡ወገግታ፡ያየ፤በጾምና፡በጸሎት፡ከእጆቹም፡ኦሪትን(ሕግን)ለተቀበለ፡ለሊቀ፡ነቢያት፡ለሙሴ፡ሰላምታ፡ይገባል።
*”ሰላም፡ለዘካርያስ፡ካህን፡ወነቢይ፡ዘርእዮ፡ለካህን፡ዐቢይ፡ዘስሙ፡ዮሴዕ፡ዘይነብር፡ውስተ፡ምሥዋዒሁ፡ለእግዚብሔር”።ትርጉም፦በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ውስጥ፡ስሙ፡ዮሴዕ፡የሚባል፡ታላቁን፡ካህን፡ተቀምጦ፡ላየው፡ለካህኑና፡ለነቢዩ፡ዘካርያስ፡ሰላምታ፡ይገባል።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ካህናቲከ፡ይለብሱ፡ጽድቀ።ወጻድቃኒከ፡ትፍሥሕተ፡ይትፌሥሑ።በእንተ፡ዳዊት፡ገብርከ”።መዝ131፥9-10፡ወይም፡መዝ57፥10-11።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ23፥29-39።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ኤጲፋንዮስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁ­ላችንም፡ይሁንልን።