ዛሬ፡መስከረም3፡ቀን (Sept 13 2018)

*እንኳን፡ለኢትዮጵያዊው፡ጻድቅ፡የስውራን፡ቅዱሳን፡አባቶች፡መኖርያ፡የሆነውን፡በሱማሌ፡ክልል፡በርሃ፡ውስጥ፡የሚገኘው፡ታላቁ፡ገዳም፡ደብረ፡ሐዘሎን፡ለመሰረቱት፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡አንበስ፡ዘአዘሎ፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለገዳመ፡ሲሐት፡ለአባ፡ሙሴ፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦የከበረ፡አባት፡ሊቀ፡ጳጳሳት፡አባ፡ዲዮናስዮስ፡ከተሾመ፡በሁለተኛው፡ዓመት፡፡በእስክድርያ፡ከተማ፡የኤጲስቆጶሳት፡የአንድነት፡ጉባኤ፡ከተደረገበት(ይህም፡ጉባኤ፡የሆነው፡ነፍስ፡ከሥጋዋ፡ጋር፡ትሞታለች፡በዕለተ፡ትንሣኤም፡ከሥጋዋ፡ጋር፡አብራ፡ትነሣለች፡ስለሚሉ፡ክፋዎች፡በዐረቢያ፡አገር፡ስለ፡ተነሡ፡ሰዎች፡ነው)፣ከሰማዕት፡አባ፡ዲዮስቆሮስ፣ሰማዕት፡ከሆነ፡ከሊቀ፡ጳጳሳት፡ዲዮናስዮስ፣ከዲያቆን፡በትንከልና፡ከብዙዎች፡ከፋርስ፡ሰማዕታት፡ከዕረፍታቸው፡መታሰቢያ፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለአባ፡አንበስ፡ዘከለሎ፡ሞገስ”።ትርጉም፦በሞገስ፡የጋረደው፡ለኾነ፡ለአባ፡አንበስ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ።
*”ሰላም፡ለአባ፡አንበስ፡በፍኖተ፡ፃማ፡ወሥራሕ።ዘይጼዓን፡ዘልፈ፡ዲበ፡አንበሳ፡መፍርህ።ለዘይጸድቅ፡ብእሲ፡ይገብእ፡ፍትሕ።ኢያጠፍኦ፡ማይ፡ወርደተ፡ዝናም፡ብዙኅ።ለዓሠረ፡ደሙ፡ቀይሕ፡ዘሀሎ፡በኰኵሕ”።ትርጉም፦በሚያደክምና፡በሚያዝል፡ጎዳና፡ላይ፡አስፈሪ፡በኾነ፡አንበሳ፡ዘወትር፡የሚጫን፡ለኾነ፡ለአባ፡አንበስ፡ሰላምታ፡ይገባል፤እውነተኛ፡ለኾነ፡ሰው፡ፍርድ፡እስኪደረግ፡ድረስ፡በዐለት፡ላይ፡ቀይ፡የደሙን፡ምልክት፡የውሃና፡የበዛ፡ዝናም፡አወራረድ፡አያጠፋውም።
*”ሰላም፡ለሙሴ፡ዘረሰየ፡እምዓለም፡ተፈልጦ።ቔጽለ፡ሆሣዕና፡አራዘ፡ወፍሬ፡ዘይቶን፡ሥብጦ።በብዙኅ፡መከራ፡እምድኅረ፡ሰይጣን፡አስፈጦ፧እግዚአብሔር፡መሐሪ፡መንገለ፡ገዳም፡ሜጦ።ኀበ፡ሥጋሁ፡የዓርፍ፡ወነፍሶ፡ይትሜጦ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም3።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”እስመ፡አድኀንካ፡ለነፍስየ፡እሞት።ወለአዕይትየኒ፡እምአንብዕ።ወለእገርየኒ፡እምዳኅፅ”።መዝ55፥13-14።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ18፥18-23።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የቅዱስ፡ዲዮስቆሮስ፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችን፡ይሁንልን።