ዛሬ፡መስከረም1፡ቀን (Sept 11 2018)

*እንኳን፡ለርእሰ፡ዓውደ፡ዓመት፡ለቅዱ­ስ፡ዮሐንስ፡አደረሰን።(ከዘመነ፡ቅዱስ፡ማርቆስ፡ወደ፡ዘመነ፡ቅዱስ፡ሉቃስ፡በሰላም፡አሸጋገረን)፣ለመላእክት፡አለቃ፡ለቅዱስ፡ራጉ­ኤል፡ለበዓለ፡ሲመቱ፣ለሐዋርያው፡ለቅ­ዱስ፡ለርተሎሜዎስ፡በዓለ፡ዕረፍቱ፣ለታ­ላቁ፡አባት፡ለቁልዝም፡ሰው፡ለሆነ፡­ፍፁም፡ፃድቅ፡ለአባ፡ሚልኪ፡በዓለ፡ዕ­ረፍት፡­፡በተጨማሪ፡በዚች፡በሰንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከሦስተኛ፡የእስክድርያ፡ሊቀ­፡ጳጳስ፡ከአባ፡ሚልዮስ፡በዓለ፡ዕረ­ፍትና፡ከቅዱስ፡ኢዮብ፡በፈሳሽ፡ውኃ፡ታጥቦ­፡ከደዌው፡ሁሉ፡ከዳነበት፡ቀን፣ረድኤት፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*”ሰላም፡ለራጉኤል፡ወለሳቁኤል፤ለአፍኒን፡ወለራሙኤል፡እለ፡የዐውዱ፡መንበሮ፡ለልዑል”።ትርጉም፦የልዑል፡ዙፋኑን፡ለሚዞሩ፡ለራጉኤልና፡ለሳቁኤል፤ለአፍኒንና፡ለራሙኤል፡ሰላምታ፡ይገባል፡፡አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ።
*”ባርክ፡ለነ፡እግዚኦ፡ዘንተ፡ዓመተ­፡ምሕረትነ፡በብዝሃ፡ኂሩትከ፡ለሕዝ­ብከ፡ኢትዮጵያ፡ከመ፡ንግነይ፡ለስም­ከ፡ቅዱስ፡ወከመ፡ይኩን፡ንብረተነ፡­በሰላም፡ወባዳኅና፡በዝንቱ፡ዓመት።­”ትርጉም፦ባርክልን፡አቤቱ፡ይህንን­፡የምሕረት፡ዓመታችን፡በቸርነትህ፡­ብዛት፡ለሕዝቦችህ፡ኢትዮጵያ፡እንድ­ንገዛ፡ለቅዱስ፡ስምህ፡እንዲሆንም፡­ኑሮዋችን፡በሰላም፡በደኅና፡በዚህ፡­ዓመት።የዕለቱ፡መዝሙር።
*”ሰአሉ፡ለነ፡ሐዋርያት፡አስራብ፡ዘወርቅ፡ወሐይዝተ፡ጽድቅ፡ወዘሐረገ፡ወይን፡አዕጹቅ፡ሰአሉ፡ለነ፡አስተምሕሩ”።ትርጉም፦የወርቅ፡ፏፏቴዎች፡የጽድቅ፡ፈሳሽና፡የወይን፡ሐረግ፡ቅርጫፎች፡ሐዋርያት፡ለምኑልን፡አማልዱን።አ­ባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በሰዓታቱ፡ላ­ይ።
*”ሰላም፡ለምልኪ፡እምዐቢይተ፡ቁልዝም፡ዘኮነ።ዘሠናየ፡ልሕቀ፡ወዘአዳመ፡ተሐፅነ።እምእግዚአብሔር፡ከሀሊ፡ነሢኦ፡ሥልጣነ።በኃይለ፡ጸሎቱ፡ቀነየ፡ሰይጣነ።እንዘ፡ያፀውሮ፡ገብላተ፡ወስቑረ፡ዕብነ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም1።
*የዕለቱ፡ዓራራይ፡ዜማ፦”አባ፡ዮሐንስ፡ባርከ፡ፍሬሃ፡ለምድር፡ቀዳማዌ፡ሣዕረ፡ደኃራዌ፡ሰብለ፡ዕተብ፡ወጸሊ፡ፍሬሃ፡ለምድር”። ትርጉም፦አባ፡ዮሐንስ፡የምድርን፡ፍሬዋን፡ባርክ፡፡መጀመሪያ፡ሳርን፡ሁለተኛም፡ሰብልን፡ባርክ፡ስለምድር፡ፍሬ፡ጸልይ።
*የዕለቱ፡ምልጣን፡ግእዝ፡ዜማ፦”ወአንተኒ፡ሕጻን፡ነቢየ፡ልዑል፡ትሰመይ፡ዓርኩ፡ለመርዓዊ፡ትሰመይ፡ወአዝማዱ፡በሥጋ፡ትሰመይ፡ተፈኖከ፡ታርኁ፡አናቅጸ፡ጽድቅ”።ትርጉም ፦አንተም፡ሕጻን፡የልዑል፡ነቢይ፡ትባላለህ፡፡ለሙሽራው፡ሚዜ፡ትባላለህ፡የሥጋ፡ዘመዱ፡ትባላለህ፡የጽድቅ፡በሮች፡እንድተፍት፡ተልከሃል።ቅዱስ፡ያሬድ፡በድጓው፡ላይ።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”አድኅነኒ­፡እምእለ፡ሮዱኒ፡እስመ፡ይኄይሉኒ።­ወአውፅአ፡እሞቅሕ፡ለነፍስየ።ከመ፡­እግነይ፡ለስምከ፡እግዚኦ”።መዝ141፥6-7፡ወይም፡መዝ64፥11-12።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ­11፥1-20።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡ቅ­ዳሴ፡ሐዋርያት፡ነው።መልካም፡አዲስ­፡ዓመትና፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።

ባርክ_ለነ

ባርክ ለነ እግዚኦ ዘንተ ዓመተ ምሕረትከ
በብዝኃ ኂሩትከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ
ከመንግነይ ለስምከ ቅዱስ/2/
ወከመ ይኩን ንብረትነ በሰላም
ወበዳኅና ለዝንቱ ዓመት/2/
ባርክልን አቤቱ ይህንን የምሕረት ዓመታችንን በቸርነትህ ብዛት ለሕዝቦችህ ኢትዮጵያ
እንድንገዛ ለቅዱስ ስምህ /2/
እንዲሆንልን ኑሮአችን በሰላም
በደኅና በዚህ ዓመት /2/

“ስዓትን በስዓት ቀንን በቀን ወራትን በወራት ዓመትን በዓመት ሁሉን በችሎቱ እያቀያየረ በቸርነቱ በሰላምና በጤና ለዚህች ዕለት ላደረሰን “ለድንግል ማርያም ልጅ ለኃያሉ አምላካችን ልዑል ቅዱስ እግዚአብሔር ” ስሙ ዘውትር በፍጥረታት ሁሉ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን አሜን !!! (“እርሱ እግዚአብሔር ነው ደስ ያሰኘውን ያድርግ”1ኛ ሳሙ፡፫፥፲፰) ለአዲሱ ዓመት እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን !!!