ዛሬ፡መስከረም5፡ቀን (Sept 15 2018)

*እንኳን፡ታላቁን፡አስገራሚውን፡ጣራዊ፡ክፍት፡ሆኖ፡ዝናብ፡የማይገባው፡ቤተ፡መቅደስ፡ለአነጹ፡ለታላቁ፡አባት፡ለአቡነ፡አሮን፡ዘመቄት(መንክራዊ)፡የዕረፍት፡በዓል፣እግዚአብሔር፡ለሚወድ፡ሃይማኖቱ፡ለቀና፡ለኢትዮጵያዊው፡ንጉሥ፡ለአፄ፡ልብነ፡ድንግል፡የዕረፍት፡በዓልና፡ለአቡነ፡ገብረ፡ኢየሱስ፡ዘጎንደር፡የልደት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን።በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከከበረች፡ሶፍያ፡ከሁለት፡ልጆቿ፣ከአክሶስናና፡ከበርናባ፡ከሚባሉት፡በሰማዕትነት፡ከዐረፋ፡ና፡ከሰማዕቱ፡ቅዱስ፡ማማስ፡ዕረፍት፡ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
*አቡነ፡ገብረ፡ኢየሱስ፡ዘጎንደር፦የትውልድ፡ሀገራቸው፡ጎንደር፡ፎገራ፡ሲሆን፡መስከረም5፡ቀን፡ተወለዱ።ጻድቁ፡የሚታወቁት፡አንድ፡ትልቅ፡ግብር፡አላቸው።እርሱም፡ጥርሳቸው፡እያበራ፡ለቤተ፡ክርስቲያን፡አገልግሎት፡ይሰጥ፡ነበር።መነኮሳቱ፡በጥርሳቸው፡ብርሃ፡ብቻ፡አገልግሎት፡ያካሄዱ፡ነበር።ጻድቁ፡ሲያርፉም፡ጥርሳቸው፡የ6፡ሰዓት፡መንገድ፡ተሂዶ፡ሲያበራ፡ታይቷል።በጻድቁ፡ስም፡የተጠሩ፡ገዳማት፡በትግራይና፡ሽሬና፡በጎንደር፡ይገኛል።ዕረፍታቸው፡መጋቢት5፡ነው።ምንጭ፡መዝገበ፡ቅዱሳንና፡ቅዱሳን፡በዓላት።
“ሰላም፡ለማማስ፡ሰማዕተ፡ወልድ፡ዘአቑረራ፡ለነድ፡ዘሎቱ፡አንበሳ፡ይሰግድ”።ትርጉም፦አንበሳ፡ለሚሰግድለትና፡ነበልባልን፡ላቀዘቀዛት፡የወልድ፡ምስክር፡ለኾነ፡ለማማስ፡ሰላምታ፡ይገባል።አባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በተአምኆ፡ቅዱሳን፡ላይ።
*”ሰላም፡እብል፡ለማማስ፡ምቱር።በስይፍተ፡መንገን፡በሊሐት፡ወበመንኰራኵር፡፡ዝንቱ፡መዋዒ፡ሶበ፡ጸለየ፡በደብር።ተውህበ፡ሎቱ፡እምሰማይ፡በትር።ወበዘቢቢጦቱ፡ማየ፡አውጽአ፡እምድር”።ትርጉም፦ስሎች፡በኾነ፡የመዘውር፡ሰይፎች፡እና፡በመንኰራኵር፡የተቆረጠ፡ለኾነ፡ለማማስ፡ሰላም፡እላለኊ፤ይኽ፡አሸናፊ፡በተራራ፡ላይ፡በጸለየ፡ጊዜ፡ከሰማይ፡ለርሱ፡በትር፡ተሰጠለት፤በምቱም፡ውሃን፡ከምድር፡አወጣ።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የመስከረም5።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”አዋልደ፡ንግሥት፡ለክብርከ።ወትቀውም፡ንግሥት፡በየማንከ።በአልባሰ፡ወርቅ፡ዑጽፍት፡ወኊብርት”።መዝ44፥9።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ13፥31-44።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የሠለስቱ፡ምዕት፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።