ዛሬ፡ጳጉሜን5፡ቀን

*እንኳን፡ከዐሥራ፡ሁለቱ፡ደቂቀ፡ነቢያት፡አንዱ፡ለሆነው፡ለታላቁ፡ነቢይ፡ለቅዱስ፡አሞጽ፡የዕረፍት፡በዓልና፡እናትና፡አባቱ፡የተውለትን፡ንብረት፡በመተው፡፡ከዓለም፡ለወጣ(ወደ፡ገዳም፡ለገባ)ከልብስ፡ተራቁቶ፡ለሚኖር፡በጸሎቱ፡ታላቁን፡አስፈሪ፡ዘንዶ፡ለማዳ፡እንስሳ፡ላደረገ፡ለታላቁ፡አባት፡ለብርቱ፡ልጅ፡አባ፡በርሱማ፡የዕረፍት፡በዓል፡በሰላም፡አደረሰን፡፡በተጨማሪ፡በዚች፡ቀን፡በስንክሳሩ፡ከሚታሰቡ፦ከንጽሕ፡ከድግል፡አባት፡ከምስር፡አገር፡ኤጲስቆጶስ፡ከአባ፡ያዕቆብ፡ዕረፍትና፡ከታላቁ፡አባት፡ከአባ፡መግደር፡ዕረፍት፡ረድኤትና፡በረከትን፡ይደርብን።
*”ሰአሉ፡ለነ፡ነቢያት፡ስኩራነ፡መንፈስ፡ምሉኣን፡ሞገስ፡አቅርንተ፡ሥሉስ፡ቅዱስ”።ትርጉም፦የሥላሴ፡ነጋሪቶች(ዐዋጅ፡ነጋሪዎች)፡የምትኾኑ፡ክብርን፡የተመላችኊ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡የተቃኛችኊ፡ነቢያት፡ለምኑልን፡ለእኛ፡አማልዱን።አ­ባ፡ጊዮርጊስ፡ዘጋስጫ፡በሰዓታቱ፡ላ­ይ።
*”ሰላም፡ለበርሱማ፡ትርሲተ፡ዓለም፡ዘገደፈ።እስከ፡ኢያጥረየ፡አሐደ፡ዐጽፈ።ወዲበ፡ዝኒ፡ወሰከ፡ፃማ፡ተጋድሎ፡ትረፈ።ከመ፡ያጽምዕ፡አመ፡ደኃሪ፡ምስለ፡ቅዱሳን፡ምዕራፈ።ማዕከ፡ሥጋሁ፡ወምድር፡ኢገብራ፡መንጸፈ”።አርከ፡ሥሉስ፡(አርኬ)የጳጉሜን5።
*የዕለቱ፡ምስባክ፦”ላዕለ፡ተኵላ፡ወከይሲ፡ትፄዐን።ወትከይድ፡አንበሳ፡ወከይሴ።እስመ፡ብየ፡ተወከለ፡አድኅኖ”።መዝ90፥13-14።የሚነበበው፡ወንጌል፡ማቴ5፥1-17፡ወይም፡ማር16፥15-19።የሚቀደሰው፡ቅዳሴ፡የሠለስቱ፡ምዕት፡ቅዳሴ፡ነው።መልካም፡በዓል፡ለሁላችንም፡ይሁንልን።